La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 37:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ዮሴ​ፍም ሕል​ምን አለመ፤ ለወ​ን​ድ​ሞ​ቹም ነገ​ራ​ቸው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ዮሴፍም ሕልም ዐለመ፤ ሕልሙንም ለወንድሞቹ ሲነግራቸው የባሰ ጠሉት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ዮሴፍም ሕልምን አለመ፥ ለወንድሞቹም ነገራቸው፥ እነርሱም እንደገና አብዝተው ጠሉት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አንድ ሌሊት ዮሴፍ ሕልም አየ፤ ሕልሙን ለወንድሞቹ በነገራቸውም ጊዜ ከቀድሞው ይበልጥ ጠሉት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ዮሴፍም ሕልምን አለመ ለወንድሞቹም ነገራቸው፤ እነርሱም እንደ ገና በብዙ ጠሉት

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 37:5
20 Referencias Cruzadas  

በዚ​ያች ሌሊ​ትም አቤ​ሜ​ሌክ ተኝቶ ሳለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሕ​ልም ወደ እርሱ መጣ፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “እነሆ፥ አንተ ስለ ወሰ​ድ​ሃት ሴት ትሞ​ታ​ለህ፤ እር​ስዋ ባለ ባል ናትና።”


ሕል​ምም አለመ፤ እነ​ሆም መሰ​ላል በም​ድር ላይ ተተ​ክሎ፥ ራሱም ወደ ሰማይ ደርሶ፥ እነ​ሆም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መላ​እ​ክት ይወ​ጡ​በ​ትና ይወ​ር​ዱ​በት ነበር።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በጎቹ በሚ​ፀ​ንሱ ጊዜ ዐይ​ኔን አን​ሥቼ በሕ​ልም አየሁ፤ እነ​ሆም፥ በበ​ጎ​ችና በፍ​የ​ሎች ላይ የሚ​ን​ጠ​ላ​ጠ​ሉት የበ​ጎ​ችና የፍ​የ​ሎች አው​ራ​ዎች ነጭ፥ ዝን​ጕ​ር​ጕ​ሮ​ችና ሐመደ ክቦ ነበሩ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሕ​ልም፦ ‘ያዕ​ቆብ ያዕ​ቆብ’ አለኝ፤ እኔም፦ ‘እነ​ሆኝ ምን​ድን ነው?’ አል​ሁት።


ወን​ድ​ሞ​ቹም አባ​ታ​ቸው ከል​ጆቹ ሁሉ ይልቅ እን​ደ​ሚ​ወ​ድ​ደው በአዩ ጊዜ ጠሉት፤ በሰ​ላም ይና​ገ​ሩ​ትም ዘንድ አል​ቻ​ሉም።


እር​ሱም አላ​ቸው፥ “እኔ ያለ​ም​ሁ​ትን ሕልም ስሙ፤


ወን​ድ​ሞ​ቹም፥ “በእኛ ላይ ልት​ነ​ግ​ሥ​ብን ይሆን? ወይስ ገዢ ትሆ​ነን ይሆን?” አሉት። እን​ደ​ገ​ናም ስለ ሕል​ሙና ስለ ነገሩ የበ​ለጠ ጠሉት።


ሁለ​ቱም በአ​ን​ዲት ሌሊት ሕል​ምን አለሙ። በግ​ዞት ቤት የነ​በ​ሩት የግ​ብፅ ንጉሥ ጠጅ አሳ​ላ​ፊ​ዎች አለ​ቃና የእ​ን​ጀራ አበ​ዛ​ዎች አለቃ ሁለ​ቱም እየ​ራ​ሳ​ቸው ሕል​ምን አለሙ።


ከሁ​ለት ዓመት በኋ​ላም ፈር​ዖን ሕል​ምን አየ፤ እነ​ሆም፥ በወ​ንዙ ዳር ቆሞ ነበር።


እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “እና​ንተ ሰላ​ዮች ናችሁ ፤ የሀ​ገ​ሩን ሁኔታ ልታዩ መጥ​ታ​ች​ኋል።”


በም​ክ​ራ​ቸው የሰ​ደ​ቡት ጌቶች ሆኑ​በት፤ ቀስ​ተ​ኞ​ችም ወጉት፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በገ​ባ​ዖን ለሰ​ሎ​ሞን በሌ​ሊት በሕ​ልም ተገ​ለ​ጠ​ለት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰሎ​ሞ​ንን፥ “እን​ድ​ሰ​ጥህ የም​ት​ፈ​ል​ገ​ውን ለምን” አለው።


“ከዚ​ህም በኋላ እን​ዲህ ይሆ​ናል፤ መን​ፈ​ሴን በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ አፈ​ስ​ሳ​ለሁ፤ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ች​ሁም ትን​ቢ​ትን ይና​ገ​ራሉ፤ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቻ​ች​ሁም ሕል​ምን ያል​ማሉ፤ ጐል​ማ​ሶ​ቻ​ች​ሁም ራእ​ይን ያያሉ፤


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለባ​ሪ​ያ​ዎቹ ለነ​ቢ​ያት ያል​ገ​ለ​ጠ​ው​ንና ያል​ነ​ገ​ረ​ውን ምንም አያ​ደ​ር​ግ​ምና።


እር​ሱም፥ “ቃሌን ስሙ፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነቢይ የሆነ ቢኖር በራ​እይ እገ​ለ​ጥ​ለ​ታ​ለሁ፤ ወይም በሕ​ልም እና​ገ​ረ​ዋ​ለሁ።


እኔ ቃል​ህን ሰጠ​ኋ​ቸው፤ ዓለም ግን ጠላ​ቸው፤ እኔ ከዓ​ለም እን​ዳ​ይ​ደ​ለሁ እነ​ርሱ ከዓ​ለም አይ​ደ​ሉ​ምና።