እነዚያ ይስማኤላውያን ነጋዴዎችም ሲያልፉ ወንድሞቹ ዮሴፍን ከጕድጓድ ጐትተው አወጡት፤ ለይስማኤላውያንም ዮሴፍን በሃያ ብር ሸጡት፤ እነርሱም ዮሴፍን ወደ ግብፅ ወሰዱት።
ዘፍጥረት 37:36 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነዚያ ይስማኤላውያን ሰዎች ግን ዮሴፍን በግብፅ ለፈርዖን ጃንደረባ ለዘበኞቹ አለቃ ለጲጥፋራ ሸጡት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ፣ የምድያም ነጋዴዎች ዮሴፍን ወደ ግብጽ ወስደው፣ ከፈርዖን ሹማምት አንዱ ለነበረው ለዘበኞች አለቃ፣ ለጲጥፋራ ሸጡት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነዚያ የምድያም ሰዎች ግን ዮሴፍን በግብጽ ለፈርዖን ጃንደረባ ለዘበኞቹ አለቃ ለጶጥፋራ ሸጡት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ የምድያም ሰዎች እስማኤላውያን ዮሴፍን በግብጽ አገር ለጶጢፋር ሸጡት፤ ጶጢፋር ከፈርዖን ባለሥልጣኖች አንዱ የሆነ የዘበኞቹ አለቃ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነዚያ የምድያም ሰዎች ግን ዮሴፍን በግብፅ ለፈርዖን ጃንደረባ ለዘበኞቹ አለቃ ለዺጥፋራ ሸጡት። |
እነዚያ ይስማኤላውያን ነጋዴዎችም ሲያልፉ ወንድሞቹ ዮሴፍን ከጕድጓድ ጐትተው አወጡት፤ ለይስማኤላውያንም ዮሴፍን በሃያ ብር ሸጡት፤ እነርሱም ዮሴፍን ወደ ግብፅ ወሰዱት።
የእስር ቤቱ ዘበኞች አለቃም ለዮሴፍ አሳልፎ ሰጣቸው፤ እርሱም ያገለግላቸው ነበር፤ በግዞት ቤትም አንድ ዓመት ተቀመጡ።
በዚያም የእንጀራ አበዛዎች አለቃ አገልጋይ የሆነ አንድ ዕብራዊ ጐልማሳ ከእኛ ጋር ነበር፤ ለእርሱም ነገርነው፤ ሕልማችንንም ተረጐመልን።
በባቢሎንም ንጉሥ በናቡከደነፆር በዐሥራ ዘጠነኛው ዓመት በአምስተኛው ወር ከወሩም በሰባተኛው ቀን በባቢሎን ንጉሥ ፊት የሚቆመው የአበዛዎች አለቃ ናቡዛርዳን ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ።
ወደ እግዚአብሔርም የተጠጋ መጻተኛ፥ “በእውነት እግዚአብሔር ከሕዝቡ ይለየኛል” አይበል፤ ጃንደረባም፥ “እነሆ፥ እኔ እንደ ደረቀ ዛፍ ነኝ” አይበል።
የአዛዦች አለቃ ናቡዛርዳንም በከተማዪቱ የቀሩትን ሕዝብ፥ ኰብልለውም ወደ እርሱ የገቡትን ሰዎችና የቀረውንም የሕዝቡን ቅሬታ ወደ ባቢሎን ማረካቸው።