La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 37:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ይሁ​ዳም ወን​ድ​ሞ​ቹን እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ወን​ድ​ማ​ች​ንን ገድ​ለን ደሙን ብን​ሸ​ሽግ ጥቅ​ማ​ችን ምን​ድን ነው?

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ይሁዳም ወንድሞቹን እንዲህ አላቸው፤ “ወንድማችንን መግደልና አሟሟቱን መደበቅ ምን ይጠቅመናል?

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ይሁዳም ወንድሞቹን እንዲህ አላቸው፦ “ወንድማችንን ገድለን ደሙን ብንሸሽግ ጥቅማችን ምንድነው?

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በዚህ ጊዜ ይሁዳ ወንድሞቹን እንዲህ አላቸው፤ “ወንድማችንን ገድለን የአሟሟቱን ሁኔታ ብንደብቅ ምን ይጠቅመናል?

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ይሁዳም ወንድሞቹን እንዲህ አላቸው፦ ወንድማችንን ገድለን ደሙን ብንሸሽግ ጥቅማችን ምንድር ነውም?

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 37:26
16 Referencias Cruzadas  

ዔሳ​ውም፥ “እነሆ፥ እኔ ልሞት ነኝ፤ ይህች ብኵ​ርና ለምኔ ናት?” አለ።


ኑ፥ እን​ግ​ደ​ለ​ውና በአ​ንድ ጕድ​ጓድ ውስጥ እን​ጣ​ለው፤ ክፉ አው​ሬም በላው እን​ላ​ለን፤ ሕል​ሞ​ቹም ምን እን​ደ​ሚ​ሆኑ እና​ያ​ለን።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለው፥ “ቃየል! ምን አደ​ረ​ግህ? የወ​ን​ድ​ምህ የአ​ቤል የደሙ ድምፅ ከም​ድር ወደ እኔ ይጮ​ሃል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃየ​ልን አለው፥ “ወን​ድ​ምህ አቤል ወዴት ነው?” ቃየ​ልም አለ፥ “አላ​ው​ቅም፤ በውኑ የወ​ን​ድሜ ጠባ​ቂው እኔ ነኝን?”


ሌቦች በስ​ውር ከዕ​ብ​ራ​ው​ያን ሀገር ሰር​ቀ​ው​ኛ​ልና፤ በዚ​ህም ደግሞ ምንም ያደ​ረ​ግ​ሁት ሳይ​ኖር በግ​ዞት ቤት አኑ​ረ​ው​ኛ​ልና።”


እነ​ር​ሱም እርስ በር​ሳ​ቸው እን​ዲህ ተባ​ባሉ፥ “በእ​ው​ነት ወን​ድ​ማ​ች​ንን በድ​ለ​ናል፤ እኛን በመ​ማ​ጠን ነፍሱ ስት​ጨ​ነቅ አይ​ተን አል​ሰ​ማ​ነ​ው​ምና፤ ስለ​ዚህ ይህ መከራ መጣ​ብን።”


እና​ንተ በእኔ ላይ ክፉ መከ​ራ​ችሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ዛሬ እንደ ሆነው ብዙ ሕዝብ እን​ዲ​መ​ገብ ለማ​ድ​ረግ ለእኔ መል​ካም መከረ።


ዳዊ​ትም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቀ​ባ​ውን እኔ ገድ​ያ​ለሁ ብሎ አፍህ በላ​ይህ መስ​ክ​ሮ​አ​ልና ደምህ በራ​ስህ ላይ ይሁን” አለው።


ነገር ግን በእጄ ዐመፅ የለም፤ ጸሎ​ቴም ንጹሕ ነው።


ተቸ​ግ​ሬ​አ​ለ​ሁና አቤቱ ይቅር በለኝ፥ ዐይ​ኔም ከቍጣ የተ​ነሣ ታወ​ከች፥ ነፍ​ሴም፥ ሆዴም።


ነገር ግን ኤል​ና​ታ​ንና ጎዶ​ልያ፥ ገማ​ር​ያም ክር​ታ​ሱን እን​ዳ​ያ​ቃ​ጥል ንጉ​ሡን ለመ​ኑት፤ እርሱ ግን አል​ሰ​ማ​ቸ​ውም።


በዚ​ያም የተ​ገኙ ዐሥር ሰዎች ቀር​በው እስ​ማ​ኤ​ልን እን​ዲህ አሉት፥ “በሜ​ዳው ድልብ አለ​ንና፥ ገብ​ስና ስንዴ፥ ዘይ​ትና ማርም አለ​ንና አት​ግ​ደ​ለን፤” እር​ሱም በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው መካ​ከል እነ​ር​ሱን መግ​ደል ተወ።


ደም​ዋም በመ​ካ​ከ​ልዋ አለ። በተ​ራ​ቈተ ድን​ጋይ ላይ አደ​ረ​ገ​ችው እንጂ በአ​ፈር ይከ​ደን ዘንድ በመ​ሬት ላይ አላ​ፈ​ሰ​ሰ​ች​ውም።


ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል?


በዚ​ያን ጊዜ ሥራ​ች​ሁም እነሆ፥ ዛሬ ታፍ​ሩ​በ​ታ​ላ​ችሁ፤ መጨ​ረ​ሻው ሞት ነውና።


“በደ​ምና በደም መካ​ከል፥ በፍ​ር​ድና በፍ​ርድ መካ​ከል፥ በመ​ቍ​ሰ​ልና በመ​ቍ​ሰል መካ​ከል፥ በክ​ር​ክ​ርና በክ​ር​ክር መካ​ከል በሀ​ገ​ርህ ውስጥ ሰዎች ስለ​ሚ​ከ​ራ​ከ​ሩ​በት ክር​ክር የሚ​ሳ​ንህ የፍ​ርድ ነገር ቢኖር፥ አንተ ተነ​ሥ​ተህ ስሙ በዚያ ይጠራ ዘንድ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ መረ​ጠው ስፍራ ትወ​ጣ​ለህ፤