ታላቂቱም ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ሞዓብ ብላ ጠራችው፤ ይህም ከአባቴ የወለድሁት ማለት ነው። እርሱም እስከ ዛሬ የሞዓባውያን አባት ነው።
ዘፍጥረት 36:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሴይር ተራራ የሚኖሩ የኤዶማውያን አባት የዔሳው ትውልድም እንዲህ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሴይር ተራራማ አገር የሚኖሩ የኤዶማውያን አባት፣ የዔሳው ዝርያዎች እነዚህ ናቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሴይር ተራራ የሚኖሩ የኤዶማውያን አባት የዔሳው ትውልድም ይህ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በተራራማው አገር በኤዶም ይኖሩ የነበሩት ኤዶማውያን ቅድመ አያት የነበረው የዔሳው ዘሮች የሚከተሉት ናቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሴይር ተራራ የሚኖሩ የኤዶማውያን አባት የዔሳው ትውልድም ይህ ነው። |
ታላቂቱም ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ሞዓብ ብላ ጠራችው፤ ይህም ከአባቴ የወለድሁት ማለት ነው። እርሱም እስከ ዛሬ የሞዓባውያን አባት ነው።
እንዲህም ብሎ አዘዛቸው፥ “ለጌታዬ ለዔሳው፦ ባሪያህ ያዕቆብ እንዲህ አለ ብላችሁ ንገሩት፦ በላባ ዘንድ በስደት ተቀመጥሁ፤ እስከ ዛሬ ድረስ ቈየሁ፤
መግዴኤል መስፍን፥ ኤራም መስፍን፤ እነዚህ በግዛታቸው ምድር በየመኖሪያቸው የኤዶም መሳፍንት ናቸው። የኤዶማውያንም አባት ይህ ዔሳው ነው።
ከስምዖንም ልጆች አምስት መቶ ሰዎች ወደ ሴይር ተራራ ሄዱ፤ አለቆቻቸውም የይሰዔ ልጆች ፥ ፈላጥያ፥ ነዓርያ፥ ረፋያ፥ ዑዝኤል ነበሩ።
የአብድዩ ራእይ። ጌታ እግዚአብሔር ስለ ኤዶምያስ እንዲህ ይላል፦ ከእግዚአብሔር ዘንድ መስማትን ሰማሁ፤ ከባቢን ወደ አሕዛብ ልኮ፥ “ተነሡ፤ በላይዋም እንነሣና እንውጋት።
የሴይርን ተራራ ለዔሳው ልጆች ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ እኔ ከምድራቸው የጫማ መርገጫ ታህል እንኳን አልሰጣችሁምና አትጣሉአቸው።
ለይስሐቅም ያዕቆብንና ዔሳውን ሰጠሁት፤ ለዔሳውም የሴይርን ተራራ ርስት አድርጌ ሰጠሁት፤ የያዕቆብም ልጆች ወደ ግብፅ ወረዱ፤ በዚያም ታላቅ ሕዝብ ሆኑ፤ በዙም፤ በረቱም፤ ግብፃውያንም መከራ አጸኑባቸው።