ዘፍጥረት 36:43 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መግዴኤል መስፍን፥ ኤራም መስፍን፤ እነዚህ በግዛታቸው ምድር በየመኖሪያቸው የኤዶም መሳፍንት ናቸው። የኤዶማውያንም አባት ይህ ዔሳው ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መግዲኤል እና ዒራም። እነዚህ በያዙት ምድር እንደየይዞታቸው የኤዶም ዘሮች የነገድ አለቆች ነበሩ። ይህም ዔሳው፣ የኤዶማውያን አባት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማግዲኤል አለቃ፥ ዒራም አለቃ፤ እነዚህ በግዛታቸው ምድር በየመኖሪያቸው የኤዶም አለቆች ናቸው። የኤዶማውያን አባት ዔሳው ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ማግዲኤልና ዒራም። በየመኖሪያ ስፍራቸው ስም የሚጠሩት የኤዶም አለቆች እነዚህ ናቸው። ይህም ዔሳው የኤዶማውያን አባት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መግዲኤል አለቃ ዒራም አለቃ፥ እነዚህ በግዛታቸው ምድር በየመኖሪያቸው የኤዶም አለቆች ናቸው። የኤዶማውያን አባት ይህ ዔሳው ነው። |
የዔሳው ልጆች መሳፍንት እነዚህ ናቸው፤ የዔሳው የበኵር ልጅ የኤልፋዝ ልጆች፤ ቴማን መስፍን፥ ኦሜር መስፍን፥ ሳፍር መስፍን፥ ቄኔዝ መስፍን፥
አሁንም እናንተ ወደዚህ የላካችሁኝ አይደላችሁም፤ እግዚአብሔር ላከኝ እንጂ፤ ለፈርዖንም እንደ አባት አደረገኝ፤ በቤቱም ሁሉ ላይ ጌታ፥ በግብፅ ምድርም ሁሉ ላይ አለቃ አደረገኝ።
ሙሴም ከቃዴስ ወደ ኤዶምያስ ንጉሥ መልእክተኞችን እንዲህ ብሎ ላከ፥ “ወንድምህ እስራኤል እንዲህ ይላል፦ ያገኘንን መከራ ሁሉ አንተ ታውቃለህ፤
የሴይርን ተራራ ለዔሳው ልጆች ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ እኔ ከምድራቸው የጫማ መርገጫ ታህል እንኳን አልሰጣችሁምና አትጣሉአቸው።