Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘኍል 20:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ሙሴም ከቃ​ዴስ ወደ ኤዶ​ም​ያስ ንጉሥ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን እን​ዲህ ብሎ ላከ፥ “ወን​ድ​ምህ እስ​ራ​ኤል እን​ዲህ ይላል፦ ያገ​ኘ​ንን መከራ ሁሉ አንተ ታው​ቃ​ለህ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ሙሴ ከቃዴስ ለኤዶም ንጉሥ እንዲህ ሲል መልእክተኞች ላከ፤ “ወንድምህ እስራኤል የሚለው ይህ ነው፤ የደረሰብን መከራ ሁሉ ምን እንደ ሆነ አንተም ታውቃለህ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ሙሴም ከቃዴስ ወደ ኤዶምያስ ንጉሥ መልእክተኞችን እንዲህ ብሎ ላከ፦ “ወንድምህ እስራኤል እንዲህ ይላል፦ የደረሰብንን መከራ ሁሉ አንተ ታውቃለህ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ሙሴ ለኤዶም ንጉሥ እንዲህ ብለው እንዲነግሩት መልእክተኞችን ከቃዴስ ላከ፤ “ወንድምህ እስራኤል እንዲህ ይላል፦ በእኛ ላይ የደረሰውን ችግር ሁሉ ሰምተሃል፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ሙሴም ከቃዴስ ወደ ኤዶምያስ ንጉሥ መልእክተኞችን እንዲህ ብሎ ላከ፦ ወንድምህ እስራኤል እንዲህ ይላል፦ ያገኘንን መከራ ሁሉ አንተ ታውቃለህ፤

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 20:14
20 Referencias Cruzadas  

“ኤዶ​ማ​ዊዉ ወን​ድ​ምህ ነውና አት​ጸ​የ​ፈው፤ ግብ​ፃ​ዊ​ዉ​ንም በሀ​ገሩ ስደ​ተኛ ነበ​ር​ህና አት​ጸ​የ​ፈው።


ወድጃችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፣ እናንተ ግን፦ በምን ወደድኸን? ብላችኋል። ዔሳው የያዕቆብ ወንድም አልነበረምን? ይላል እግዚአብሔር ያዕቆብንም ወደድሁ፥ ዔሳውንም ጠላሁ።


እነ​ር​ሱም አሉት፥ “በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም እጅግ ከራቀ ሀገር ባሪ​ያ​ዎ​ችህ መጥ​ተ​ናል፤ ዝና​ው​ንም፥ በግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንም ያደ​ረ​ገ​ውን ሁሉ፥


ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፈ​ር​ዖ​ንና በግ​ብ​ፃ​ው​ያን ላይ ስለ እስ​ራ​ኤል ያደ​ረ​ገ​ውን ሁሉ፥ በመ​ን​ገ​ድም ያገ​ኛ​ቸ​ውን ድካም ሁሉ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ አዳ​ና​ቸው ለአ​ማቱ ነገ​ረው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አላት፥ “ሁለት ሕዝ​ቦች በማ​ኅ​ፀ​ንሽ አሉ፤ ሁለ​ቱም ሕዝብ ከሆ​ድሽ ይወ​ለ​ዳሉ፤ ሕዝ​ብም ከሕ​ዝብ ይበ​ረ​ታል፤ ታላ​ቁም ለታ​ናሹ ይገ​ዛል።”


ገሥ​ግ​ሠ​ውም በቃ​ዴስ ፋራን ምድረ በዳ ወዳ​ሉት ወደ ሙሴና ወደ አሮን፥ ወደ እስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ማኅ​በር ሁሉ ደረሱ፤ ወሬ​ው​ንም ለእ​ነ​ር​ሱና ለማ​ኅ​በሩ ሁሉ ነገ​ሩ​አ​ቸው፤ የም​ድ​ሪ​ቱ​ንም ፍሬ አሳ​ዩ​አ​ቸው።


አባ​ቶ​ቻ​ችን ወደ ግብፅ ወረዱ፤ በግ​ብ​ፅም እጅግ ዘመን ተቀ​መ​ጥን፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም እኛ​ንና አባ​ቶ​ቻ​ች​ንን በደሉ።


ከቃ​ዴ​ስም ተጓዙ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ማኅ​በር ሁሉ በሖር ተራራ ሰፈሩ።


ሰዎ​ቹ​ንም እን​ዲህ አለ​ቻ​ቸው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምድ​ሪ​ቱን አሳ​ልፎ እንደ ሰጣ​ችሁ ዐወ​ቅሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እና​ን​ተን መፍ​ራ​ት​ን በ​ላ​ያ​ችን አም​ጥ​ት​ዋ​ልና፥ በም​ድ​ሪ​ቱም የሚ​ኖ​ሩት ሁሉ ከፊ​ታ​ችሁ የተ​ነሣ ቀል​ጠ​ዋ​ልና።


ከግ​ብፅ ምድር በወ​ጣ​ችሁ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የኤ​ር​ት​ራን ባሕር በፊ​ታ​ችሁ እን​ዳ​ደ​ረቀ፥ በዮ​ር​ዳ​ኖ​ስም ማዶ በነ​በ​ሩት፥ እና​ን​ተም ፈጽ​ማ​ችሁ ባጠ​ፋ​ች​ኋ​ቸው በሁ​ለቱ በአ​ሞ​ራ​ው​ያን ነገ​ሥ​ታት፥ በሴ​ዎ​ንና በዐግ ያደ​ረ​ጋ​ች​ሁ​ትን ሰም​ተ​ናል።


በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶም በነ​በ​ሩት በሁ​ለቱ በአ​ሞ​ሬ​ዎን ነገ​ሥት በሐ​ሴ​ቦን ንጉሥ በሴ​ዎን፥ በአ​ስ​ታ​ሮ​ትና በኤ​ድ​ራ​ይን በነ​በ​ረው በባ​ሳን ንጉሥ በዐግ ያደ​ረ​ገ​ውን ሁሉ ሰም​ተ​ናል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦“ወን​ድ​ሙን በሰ​ይፍ አሳ​ድ​ዶ​ታ​ልና፥ በም​ድር ላይም ማኅ​ፀ​ንን አር​ክ​ሶ​አ​ልና፥ የሚ​ዘ​ል​ፈ​ው​ንና የሚ​ያ​ስ​ደ​ነ​ግ​ጠ​ውን በር​ብ​ሮ​አ​ልና፥ መዓ​ቱ​ንም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ጠብ​ቆ​አ​ልና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የኤ​ዶ​ም​ያስ ኀጢ​አት መቅ​ሠ​ፍ​ቴን ከማ​ድ​ረግ አል​መ​ለ​ስ​ላ​ቸ​ውም።


የበ​ኵር ልጅ​ዋም ወጣ፤ እንደ ጽጌ​ረ​ዳም ቀይ ነበረ፤ ሁለ​ን​ተ​ና​ውም ጠጕ​ራም ነበር፤ ስሙ​ንም ዔሳው ብላ ጠራ​ችው።


ከዚ​ያም በኋላ ወን​ድሙ ወጣ፤ በእ​ጁም የዔ​ሳ​ውን ተረ​ከዝ ይዞ ነበር፤ ስሙ​ንም ያዕ​ቆብ ብላ ጠራ​ችው። ርብቃ ዔሳ​ው​ንና ያዕ​ቆ​ብን በወ​ለ​ደ​ቻ​ቸው ጊዜ ይስ​ሐቅ ስድሳ ዓመት ሆኖት ነበር።


ያዕ​ቆ​ብም፥ “ስም​ህን ንገ​ረኝ” ብሎ ጠየ​ቀው። እር​ሱም፥ “ስሜን ለምን ትጠ​ይ​ቃ​ለህ? ድንቅ ነውና” አለው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios