ዘፍጥረት 36:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዔሳው ልጆች መሳፍንት እነዚህ ናቸው፤ የዔሳው የበኵር ልጅ የኤልፋዝ ልጆች፤ ቴማን መስፍን፥ ኦሜር መስፍን፥ ሳፍር መስፍን፥ ቄኔዝ መስፍን፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዔሳው ዝርያዎች እነዚህ የነገድ አለቆች ነበሩ፤ የዔሳው የበኵር ልጅ የኤልፋዝ ልጆች፦ አለቃ ቴማን፣ አለቃ ኦማር፣ አለቃ ስፎ፣ አለቃ ቄኔዝ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዔሳው መጀመሪያ ልጅ የኤልፋዝ ልጆች፥ የዔሳው ልጆች አለቆች እነዚህ ናቸው፥ የቴማን አለቃ፥ ኦማር አለቃ፥ ስፎ አለቃ፥ ቄናዝ አለቃ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዔሳው መጀመሪያ ልጅ የኤልፋዝ ነገድ አለቆች፦ ቴማን፥ ኦማር፥ ጸፎ፥ ቀናዝ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዔሳው ልጆች አለቆች እነዚህ ናቸው ለዔሳው የበኵር ለኤፋዝ ልጆች ቴማን አለቃ እማር አለቃ ስፎ አለቃ ቄኔዝ አለቃ |
ቆሬ መስፍን፥ ጎቶን መስፍን፥ አማሌቅ መስፍን፤ በኤዶም ምድር የኤልፋዝ መሳፍንት እነዚህ ናቸው፤ እነዚህ የሓዳሶ ልጆች ናቸው ።
የዔሳው ሚስት የኤሌባማ ልጆች መሳፍንት እነዚህ ናቸው፤ ዮሔል መስፍን፥ ይጉሜል መስፍን፥ ቆሬ መስፍን፤ የዔሳው ሚስት የሐና ልጅ የኤሌባማ ልጆች መሳፍንት እነዚህ ናቸው።
ሦስቱም የኢዮብ ወዳጆች ይህን የደረሰበትን ክፉ ነገር ሁሉ ሰምተው ከየሀገራቸው ወደ እርሱ መጡ፤ እነርሱም ቴማናዊው ንጉሥ ኤልፋዝ፥ አውኬናዊው መስፍን በልዳዶስ፥ አሜናዊው ንጉሥ ሶፋር ነበሩ። እነርሱም ሊጐበኙትና ሊያጽናኑት በአንድነት ወደ እርሱ መጡ።
ስለዚህ እግዚአብሔር በኤዶምያስ ላይ የመከረባትን ምክር፥ በቴማንም በሚኖሩ ስዎች ላይ ያሰባትን ዐሳብ ስሙ፤ ትንንሾች በጎችን ዘርፈው ይወስዷቸዋል፤ የሚኖሩባትንም ማደሪያቸውን ባድማ ያደርጉባቸዋል።
ስለ ኤዶምያስ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “በውኑ በቴማን ጥበብ የለምን? ከብልሃተኞችስ ምክር ጠፍቶአልን? ጥበባቸውስ አልቆአልን?
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እጄን በኤዶምያስ ላይ እዘረጋለሁ፤ ከእርስዋም ዘንድ ሰውንና እንስሳን አጠፋለሁ፤ ባድማም አደርጋታለሁ፤ ከቴማንና ከድዳንም ያመለጡ በሰይፍ ይወድቃሉ።