ዘፍጥረት 34:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብዙ ማጫ አምጣ በሉኝ፤ በምትጠይቁኝም መጠን እሰጣለሁ፤ ይህችን ብላቴና ግን ሚስት ትሆነኝ ዘንድ ስጡኝ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጥሎሽ ብትሉኝ ጥሎሽ፣ ስጦታ ብትሉም የፈለጋችሁትን ያህል እሰጣለሁ፤ ብቻ ልጅቱን እንዳገባ ፍቀዱልኝ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብዙ ጥሎሽና ስጦታ አምጣ በሉኝ፥ ይህችን ልጅ እንዳገባ ስጡኝ እንጂ፥ በነገራችሁኝም መጠን እሰጣለሁ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለሙሽራዋም ጥሎሽ የፈለጋችሁትን ያኽል ጠይቁኝ፤ እርስዋን እንዳገባ ፍቀዱልኝ እንጂ፥ የፈለጋችሁትን ሁሉ ለመስጠት ዝግጁ ነኝ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብዙ ማጫን እጅ መንሻ አምጣ በሉኝ በነገራችሁኝም መጠን እሰጣለሁ ይህችን ብላቴና ግን አጋቡኝ። |
ያዕቆብም ራሔልን ወደዳት፤ ያዕቆብም ላባን እንዲህ አለው፥ “ስለ ታናሺቱ ልጅህ ስለ ራሔል ሰባት ዓመት እገዛልሃለሁ። ሚስት ትሆነኝ ዘንድ እርስዋን ስጠኝ” አለው።
ለአንተ ቤት የተገዛሁልህ ዛሬ ሃያ አንድ ዓመት ነው፤ ዐሥራ አራት ዓመት ስለ ሁለቱ ሴቶች ልጆችህ፥ ሰባት ዓመት ስለ በጎችህ ተገዛሁልህ፤ ደመወዜንም ዐሥር ጊዜ ለዋወጥኸው።
ዳዊትም ወደ ሳኦል ልጅ ወደ ኢያቡስቴ፥ “በመቶ ፍልስጥኤማውያን ሸለፈት ያጨኋትን ሚስቴን ሜልኮልን መልስልኝ” ብሎ መልእክተኞችን ላከ።
የሳኦልም ብላቴኖች ይህን ቃል በዳዊት ጆሮ ተናገሩ፤ ዳዊትም፥ “እኔ የተዋረድሁና ክብር የሌለኝ ሰው ስሆን ለንጉሥ አማች እሆን ዘንድ ለእናንተ ትንሽ ነገር ይመስላችኋልን?” አለ።