ዘፍጥረት 33:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም መሠውያዉን አቆመ፤ የእስራኤልንም አምላክ ጠራ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያም መሠዊያ አቁሞ፣ ኤል ኤሎሄ እስራኤል ብሎ ጠራው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እዚያም መሠውያውን አቆመ፥ ያንም ኤል ኤሎሄ እስራኤል ብሎ ጠራው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እዚያም መሠዊያ ሠራና “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር” ብሎ ጠራው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም መሠውያውን አቆመ ያንም፥ ኤል ኤሎሄ እስራኤል ብሎ ጠራው። |
አብርሃምም በዐዘቅተ መሐላ አጠገብ የተምር ዛፍን ተከለ፤ በዚያም የዘለዓለሙን አምላክ የእግዚአብሔርን ስም ጠራ።
አለውም፥ “ከእንግዲህ ወዲህ ስምህ እስራኤል ይባል እንጂ ያዕቆብ አይባል፤ ከእግዚአብሔርና ከሰው ጋር ታግለህ በርትተሃልና።”
በዚያም መሠውያዉን ሠራ፤ የዚያንም ቦታ ስም ቤቴል ብሎ ጠራው፤ እርሱ ከወንድሙ ከዔሳው ፊት በሸሸበት ጊዜ እግዚአብሔር በዚያ ተገልጦለት ነበርና።
ኖኅም ለእግዚአብሔር መሠውያዉን ሠራ፥ ከንጹሕም እንስሳ ሁሉ፥ ከንጹሓን ወፎችም ሁሉ ወሰደ፤ በመሠውያውም ላይ መሥዋዕትን አቀረበ።
ንጉሡ ዳዊትም በጉባኤው ሁሉ ፊት እግዚአብሔርን አመሰገነ፤ እንዲህም አለ፥ “አቤቱ፥ የእስራኤል አምላክ አባታችን እግዚአብሔር ሆይ፥ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ቡሩክ ነህ።