እርሱም፥ “ቀኑ ገና ቀትር ነው፥ ከብቶቹ የሚሰበሰቡበት ሰዓቱም ገና አልደረሰም፤ አሁንም በጎቹን አጠጡና ሄዳችሁ አሰማሩአቸው” አላቸው።
ዘፍጥረት 29:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እርሱ ደኅና ነውን?” አላቸው። እነርሱም፥ “አዎ ደኅና ነው፤ አሁንም ልጁ ራሔል የአባቷን በጎች ይዛ ትመጣለች” አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያዕቆብም፣ “ለመሆኑ ደኅና ነው?” አላቸው። እነርሱም፣ “አዎን ደኅና ነው፤ ልጁም ራሔል እነሆ፤ በጎች እየነዳች በመምጣት ላይ ናት” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱ፦ “ደኅና ነውን?” አላቸው። እነርሱም፦ “አዎን ደኅና ነው፥ አሁንም ልጁ ራሔል ከበጎች ጋር መጣች” አሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱም “ለመሆኑ እርሱ ደኅና ነውን?” አላቸው። እነርሱም “አዎ፥ ደኅና ነው፤ እንዲያውም ልጁ ራሔል ያቺውልህ በጎች እየነዳች በመምጣት ላይ ነች” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱ፦ ደኅና ነው? አላቸው እነርሱም፦ አዎን ደኅና ነው፤ አሁንም ልጁ ራሔል ከበጎች ጋር መጣች አሉት። |
እርሱም፥ “ቀኑ ገና ቀትር ነው፥ ከብቶቹ የሚሰበሰቡበት ሰዓቱም ገና አልደረሰም፤ አሁንም በጎቹን አጠጡና ሄዳችሁ አሰማሩአቸው” አላቸው።
እርሱም፥ “ሄደህ ወንድሞችህና በጎቹ ደኅና እንደ ሆኑ እይ፤ ወሬአቸውንም አምጣልኝ” አለው። ወደ ኬብሮንም ቆላ ላከው፤ ወደ ሴኬምም መጣ።
እርሱም ደኅንነታቸውን ጠየቃቸው፤ እንዲህም አለ፥ “የነገራችሁኝ ሽማግሌ አባታችሁ ደኅና ነውን? ገና በሕይወት አለን?”
ለምድያምም ካህን ሰባት ሴቶች ልጆች ነበሩት፤ የአባታቸውንም የዮቶርን በጎች ይጠብቁ ነበር፤ እነርሱም መጥተው ውኃ ቀዱ፤ የአባታቸውንም የዮቶርን በጎች ሊያጠጡ የውኃዉን ገንዳ ሞሉ።