“እጅህን በእጄ ላይ አድርግ፤ እኔም አብሬ ከምኖራቸው ከከነዓን ሴቶች ልጆች ለልጄ ለይስሐቅ ሚስት እንዳትወስድለት በሰማይና በምድር አምላክ በእግዚአብሔር አምልሃለሁ፤
ዘፍጥረት 26:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም አሉት፥ “እኛ የጠላንህ አይደለም፤ በመልካም አኑረን፥ በመልካም አሰናበትንህ እንጂ፥ አሁንም አንተ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ቡሩክ ነህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም እንዲህ አሉ፤ “እግዚአብሔር ከአንተ ጋራ መሆኑን በግልጽ ተረድተናል፤ ስለዚህም፣ ‘በመሐላ የጸና ውል በመካከላችን መኖር አለበት’ አልን፤ ይህም በእኛና በአንተ መካከል የሚጸና ውል ነው፤ አሁንም ከአንተ ጋራ ስምምነት እናድርግ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም፤ “ጌታ ከአንተ ጋር መሆኑን በግልጥ አየን፤ ስለዚህ በእኛና በአንተ መካከል መሐላ ይኑር፤ ከአንተ ጋር ቃል ኪዳን እንጋባ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱለት፤ “እግዚአብሔር ከአንተ ጋር መሆኑን በግልጥ ዐውቀናል፤ ስለዚህ በእኛና በአንተ መካከል በሰላም ለመኖር የሚያስችል ስምምነት በመሐላ ለመፈጸም አስበናል፤ በዚህም መሠረት ቃል ኪዳን እንድትገባልን የምንፈልገው፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም አሉት፦ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር እንዳለ በእርግጥ አየን፤ |
“እጅህን በእጄ ላይ አድርግ፤ እኔም አብሬ ከምኖራቸው ከከነዓን ሴቶች ልጆች ለልጄ ለይስሐቅ ሚስት እንዳትወስድለት በሰማይና በምድር አምላክ በእግዚአብሔር አምልሃለሁ፤
ጌታውም እግዚአብሔር ከዮሴፍ ጋር እንዳለ፥ እርሱ የሚሠራውንም ሁሉ እግዚአብሔር በእጁ እንዲያከናውንለት አየ።
እንዲህም ሆነ፤ በቤቱ ባለውም ሁሉ ላይ ከሾመው በኋላ እግዚአብሔር የግብፃዊውን ቤት በዮሴፍ ምክንያት ባረከው። የእግዚአብሔርም በረከት በቤቱም፥ በእርሻውም ባለው ሁሉ ላይ ሆነ።
የዳዊት ልጅ ሰሎሞንም በመንግሥቱ በረታ፤ አምላኩም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረ፤ እጅግም አከበረው፤ አገነነውም።
አምላኩም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር እንደ ሆነ ባዩ ጊዜ ከእስራኤል ዘንድ ብዙ ሰዎች ወደ እርሱ ተጠግተው ነበርና እርሱ ይሁዳንና ብንያምን ሁሉ፥ ከኤፍሬምና ከምናሴም፥ ከስምዖንም ፈልሰው ከእነርሱ ጋር የተቀመጡትን ሰበሰበ።
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ግብፅና የኢትዮጵያ ንግዶች ደከሙ፤ ቁመተ ረዥሞች የሳባ ሰዎች ወደ አንተ ያልፋሉ፤ ለአንተም ይገዙልሃል፤ እጆቻቸውን ታስረው በኋላህ ይከተሉሃል፤ በፊትህም ያልፋሉ፤ ለአንተም እየሰገዱ፦ በእውነት እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው፤ ከእርሱም ሌላ አምላክ የለም ብለው ይለምኑሃል።
የአስጨናቂዎችሽም ልጆች እየተንቀጠቀጡ ወደ አንቺ ይመጣሉ፤ የናቁሽም ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ፤ የእስራኤል ቅዱስ የእግዚአብሔር ከተማ፥ ጽዮን ተብለሽም ትጠሪያለሽ።
እናንተ ግን የእግዚአብሔር ካህናት ትባላላችሁ፤ የአምላካችንም አገልጋዮች ተብላችሁ ትጠራላችሁ፤ የአሕዛብን ሀብት ትበላላችሁ፤ በሀብታቸውም ትመካላችሁ።
ዘራቸው በአሕዛብ መካከል፥ ልጆቻቸውም በወገኖች መካከል የታወቁ ይሆናሉ፤ ያያቸው ሁሉ እግዚአብሔር የባረካቸው ዘር እንደ ሆኑ ያውቃል፤
በልባቸው የደበቁትም ይገለጣል፤ ከዚህ በኋላ ያ የማያምነው ተመልሶ ይጸጸታል፤ በግንባሩም ወድቆ ለእግዚአብሔር ይሰግዳል፥ በእውነት እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር እንዳለም ይናገራል።
እግዚአብሔርም ኢያሱን፥ “ከሙሴ ጋር እንደ ሆንሁ እንዲሁ ከአንተ ጋር መሆኔን ያውቁ ዘንድ በዚህ ቀን በእስራኤል ልጆች ሁሉ ፊት ከፍ ከፍ አደርግህ ዘንድ እጀምራለሁ።
እንዲህም ሆነ፤ ከአንድ ወር በኋላ አሞናዊው ናዖስ መጣ፤ በኢያቢስ ገለዓድም ሰፈረ፤ የኢያቢስም ሰዎች ሁሉ፥ “አሞናዊውን ናዖስን ቃል ኪዳን አድርግልን፤ እኛም እንገዛልሃለን” አሉት።