ዘፍጥረት 25:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮቃጤንም ሶቤቅን፥ ቲማንንና ድዳንን ወለደ። የድዳንም ልጆች ራጉኤል፥ ንበከዝ፥ እስራኦምና ሎአም ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዮቅሳንም ሳባንና ድዳንን ወለደ፤ የድዳንም ልጆች፦ አሦራውያን፣ ለጡሳውያንና ለኡማውያን ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮቅሻንም ሳባንና ድዳንን ወለደ። የድዳንም ልጆች አሹራውያን፥ ለጡሻውያንና፥ ለኡማውያን ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮቅሻንም ሳባንና ደዳንን ወለደ፤ የደዳንም ዘሮች አሹራውያን፥ ሌጡሻውያንና ሌኡማውያን ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዩቅሳንም ሳባንና ድዳንን ወለደ። የድዳንም ልጆች አሦርያውያን ለጡሳውያን ለኡማውያን ናቸው፥ |
የሳባም ንግሥት የሰሎሞንን ስም፥ የእግዚአብሔርንም ስም በሰማች ጊዜ ሰሎሞንን በእንቆቅልሽ ትፈትነው ዘንድ መጣች።
የግመሎች መንጋ ወደ አንቺ ይመጣሉ፤ የምድያምና የኤፋ ግመሎች ይሸፍኑሻል፤ ሁሉ ከሳባ ወርቅንና ዕጣንን ይዘው ይመጣሉ፤ የእግዚአብሔርንም ማዳን ያበሥራሉ።
እናንተ በድዳን የምትኖሩ ሆይ! የዔሳውን ጥፋት፥ የምጐበኝበትን ጊዜ አመጣበታለሁና ሽሹ፤ ወደ ኋላም ተመለሱ፤ በጥልቅም ጕድጓድ ውስጥ ተቀመጡ።
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እጄን በኤዶምያስ ላይ እዘረጋለሁ፤ ከእርስዋም ዘንድ ሰውንና እንስሳን አጠፋለሁ፤ ባድማም አደርጋታለሁ፤ ከቴማንና ከድዳንም ያመለጡ በሰይፍ ይወድቃሉ።
የሮድያን ልጆችም ነጋዴዎችሽ ነበሩ፥ ብዙ የሆኑ የደስያት ሰዎችም የዝኆን ጥርስ ይነግዱልሽ ነበር፤ ከዚያም የመጡ ሰዎች ዋጋሽን ይሰጡሽ ነበር።
ከባሳን ኮምቦል መቅዘፊያሽን ሠርተዋል፤ መቅደስሽንም በዝኆን ጥርስ ሠሩ፤ ከኪቲም ደሴቶች ዛፍም ቤቶችሽን ሠርተዋል።