ለባሪያህ በአደረግኸው በምሕረትህና በእውነትህም ሁሉ በጎውን አድርግልኝ፤ በትሬን ብቻ ይዤ ይህን ዮርዳኖስን ተሻግሬ ነበርና፥ አሁን ግን የሁለት ክፍል ሠራዊት ሆንሁ።
ዘፍጥረት 24:49 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም ቸርነትንና እውነትን ለጌታዬ ትሠሩ እንደ ሆነ ንገሩኝ፤ ይህም ባይሆን ንገሩኝ፤ ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ እመለስ ዘንድ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ አሁን ለጌታዬ በጎነትና ታማኝነት የምታሳዩ ከሆነ ሐሳባችሁን አስታውቁኝ፤ ካልሆነ ግን ቍርጡን ንገሩኝና የምሄድበትን ልወስን።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁንም ቸርነትና እውነት ለጌታዬ ትሠሩ እንደሆነ ንገሩኝ፥ ይህም ባይሆን ንገሩኝ፥ ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ እል ዘንድ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲህ የጌታዬን ዐደራ በእውነት ተቀብላችሁ እርሱን ደስ ለማሰኘት የምትፈቅዱ እንደ ሆነ ንገሩኝ፤ የማትፈቅዱም እንደ ሆነ ቊርጡን ንገሩኝ፤ እኔም እግዚአብሔር ወደሚመራኝ እሄዳለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁንም ቸርንትና እውነት ለጌታዬ ትሠሩ እንደ ሆነ ንገሩኝ፤ ይህም ባይሆን ንገሩኝ ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ እል ዘንድ። |
ለባሪያህ በአደረግኸው በምሕረትህና በእውነትህም ሁሉ በጎውን አድርግልኝ፤ በትሬን ብቻ ይዤ ይህን ዮርዳኖስን ተሻግሬ ነበርና፥ አሁን ግን የሁለት ክፍል ሠራዊት ሆንሁ።
የእስራኤልም የሞቱ ቀን ቀረበ፤ ልጁን ዮሴፍንም ጠርቶ እንዲህ አለው፥ “በፊትህ ሞገስን አግኝቼ እንደ ሆንሁ እጅህን በጕልበቴ ላይ አድርግ፤ በግብፅ ምድርም እንዳትቀብረኝ ምሕረትንና እውነትን አድርግልኝ፤
እባክህ፥ በምድርህ ላይ እንለፍ፤ ወደ እርሻም ወደ ወይንም አንገባም፤ ከጕድጓዶችም ውኃን አንጠጣም፤ በንጉሡ ጎዳና እንሄዳለን፤ ዳርቻህንም እስክናልፍ ድረስ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አንልም።”
ሰዎቹም፥ “ሕይወታችንን ስለ እናንተ አሳልፈን ለሞት እንሰጣለን” አሉ፤ እርስዋም አለች፥ “እግዚአብሔር ምድሪቱን በሰጣችሁ ጊዜ ቸርነትንና ጽድቅን ታደርጉልናላችሁ።” ሰዎቹም፥ “ይህን ነገራችንን ባትገልጪ እግዚአብሔር ሀገራችሁን በእውነት አሳልፎ ከሰጠን ከአንቺ ጋር ቸርነትን እናደርጋለን” አሏት።