ዘፍጥረት 24:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰውዬውም ወደ ቤት ገባ፤ ግመሎቹንም አራገፈ፤ ለግመሎቹም ሣርና ገለባ አቀረቡላቸው፤ እግሩን ይታጠብ ዘንድ ውኃ አመጡለት፤ ከእርሱ ጋር ላሉ ሰዎችም አመጡላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰውየው ከላባ ጋራ ወደ ቤት ሄደ፤ የግመሎቹ ጭነት ተራግፎ ገለባና ድርቈሽ ተሰጣቸው፤ ለርሱና ዐብረውት ለነበሩት ሰዎች የእግር ውሃ ቀረበላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰውዬውም ወደ ቤት ገባ፥ ግመሎቹንም አራገፈ፥ ገለባና ገፈራም ለግመሎቹ አቀረበ፥ እግሩን ይታጠብ ዘንድ፥ ከእርሱም ጋር ላሉት ሰዎች እግር ውኃ አቀረበ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ሰውየው ወደ ቤት ሄደ፤ ላባም በግመሎቹ ላይ የነበረውን ጭነት አራግፎ ገለባና ድርቆሽ አቀረበላቸው፤ ቀጥሎም የአብርሃም አገልጋይና አብረውት የነበሩት ሰዎች እግራቸውን የሚታጠቡበት ውሃ አመጣላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰውዮውም ወደ ቤት ገባ ግመሎቹንም አራገፈ ገለባና ገፈራም ለግመሎቹ አቀረበ፤ እግሩን ይታጠብ ዘንድ ከእርሱም ጋር ላሉት ሰዎች እግር ውኃ አቀረበ። |
አላቸውም፥ “ጌቶች ሆይ፥ ወደ ባሪያችሁ ቤት ገብታችሁ እደሩ፤ እግራችሁንም ታጠቡ፤ ነገም ማልዳችሁ መንገዳችሁን ትሄዳላችሁ።” እነርሱም፥ “በአደባባዩ እናድራለን እንጂ፥ አይሆንም” አሉት።
ይበላም ዘንድ እንጀራን አቀረቡለት፤ እርሱ ግን “ነገሬን እስክናገር ደረስ አልበላም” አለ። እነርሱም “ተናገር” አሉት።
ላባም የእኅቱን የርብቃን ልጅ የያዕቆብን ስም በሰማ ጊዜ ሊቀበለው ሮጠ፥ አቅፎም ሳመው፥ ወደ ቤቱም አገባው። ነገሩንም ሁሉ ለላባ ነገረው።
ወደ ሴቲቱም ዘወር ብሎ ስምዖንን እንዲህ አለው፥ “ይህቺን ሴት ታያታለህን? እኔ ወደ ቤትህ ገባሁ፤ ለእግሮች ውኃ ስንኳ አልሰጠኸኝም፤ እርስዋ ግን አልቅሳ በእንባዋ እግሬን አራሰች፤ በጠጕርዋም አበሰች።
ልጆችን በማሳደግ፥ እንግዶችንም በመቀበል፥ የቅዱሳንንም እግሮች በማጠብ፥ የተጨነቁትንም በመርዳት፥ በጎንም ሥራ ሁሉ በመከተል፥ ይህን መልካም ሥራ በማድረግ የተመሰከረላት ልትሆን ይገባል።
ተነሥታም በግንባርዋ በምድር ወድቃ ሰገደችና፥ “እነሆ፥ እኔ ገረድህ የጌታዬን ሎሌዎች እግር አጥብ ዘንድ አገልጋይ ነኝ” አለች።