Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፍጥረት 43:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ስም​ዖ​ን​ንም ወደ እነ​ርሱ አወ​ጣ​ላ​ቸው። እግ​ራ​ቸ​ው​ንም ሊታ​ጠቡ ውኃ አመ​ጣ​ላ​ቸው፤ ለአ​ህ​ዮ​ቻ​ቸ​ውም ገፈራ ሰጣ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 የቤቱ አዛዥ ሰዎቹን ወደ ዮሴፍ ቤት አስገብቶ እግራቸውን የሚታጠቡበት ውሃ አቀረበላቸው፤ ለአህዮቻቸውም የሚበሉት ገፈራ ሰጣቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ከዚያም ስምዖንን አውጥቶ አገናኛቸው። የቤቱ አዛዥ ሰዎቹን ወደ ዮሴፍ ቤት አስገብቶ እግራቸውን የሚታጠቡበት ውሃ አቀረበላቸው፤ ለአህዮቻቸውም የሚበሉት ገፈራ ሰጣቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 የቤቱ አዛዥ ወንድማማቾቹን ወደ ዮሴፍ ቤት አስገባቸውና እግራቸውን የሚታጠቡበት ውሃ ሰጣቸው፤ ለአህዮቻቸውም ገፈራ ሰጣቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ስምዖንም አወጣላቸው። ሰውዮውም እነዚያን ስዎች ወደ ዮሴፍ ቤት አስገባቸው ውኃ አመጣላቸው እግራቸውንም ታጠቡ ለአህዮቻቸው አበቅ ስጣቸው።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 43:24
7 Referencias Cruzadas  

ውኃ እና​ም​ጣ​ላ​ችሁ፤ እግ​ራ​ች​ሁ​ንም እን​ጠ​ባ​ችሁ።


አላ​ቸ​ውም፥ “ጌቶች ሆይ፥ ወደ ባሪ​ያ​ችሁ ቤት ገብ​ታ​ችሁ እደሩ፤ እግ​ራ​ች​ሁ​ንም ታጠቡ፤ ነገም ማል​ዳ​ችሁ መን​ገ​ዳ​ች​ሁን ትሄ​ዳ​ላ​ችሁ።” እነ​ር​ሱም፥ “በአ​ደ​ባ​ባዩ እና​ድ​ራ​ለን እንጂ፥ አይ​ሆ​ንም” አሉት።


ሰው​ዬ​ውም ወደ ቤት ገባ፤ ግመ​ሎ​ቹ​ንም አራ​ገፈ፤ ለግ​መ​ሎ​ቹም ሣርና ገለባ አቀ​ረ​ቡ​ላ​ቸው፤ እግ​ሩን ይታ​ጠብ ዘንድ ውኃ አመ​ጡ​ለት፤ ከእ​ርሱ ጋር ላሉ ሰዎ​ችም አመ​ጡ​ላ​ቸው።


ዳዊ​ትም ኦር​ዮን፥ “ወደ ቤትህ ሂድ፤ እግ​ር​ህ​ንም ታጠብ” አለው። ኦር​ዮም ከን​ጉሡ ቤት ሲወጣ አንድ የን​ጉሥ መል​እ​ክ​ተኛ ተከ​ተ​ለው።


ወደ ሴቲ​ቱም ዘወር ብሎ ስም​ዖ​ንን እን​ዲህ አለው፥ “ይህ​ቺን ሴት ታያ​ታ​ለ​ህን? እኔ ወደ ቤትህ ገባሁ፤ ለእ​ግ​ሮች ውኃ ስንኳ አል​ሰ​ጠ​ኸ​ኝም፤ እር​ስዋ ግን አል​ቅሳ በእ​ን​ባዋ እግ​ሬን አራ​ሰች፤ በጠ​ጕ​ር​ዋም አበ​ሰች።


ልጆችን በማሳደግ፥ እንግዶችንም በመቀበል፥ የቅዱሳንንም እግሮች በማጠብ፥ የተጨነቁትንም በመርዳት፥ በጎንም ሥራ ሁሉ በመከተል፥ ይህን መልካም ሥራ በማድረግ የተመሰከረላት ልትሆን ይገባል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos