የእግዚአብሔርን ፋሲካ ያደርግ ዘንድ ወደ እናንተ የመጣ መጻተኛ ቢኖር ወንዱን ሁሉ ትገርዛለህ፤ ያን ጊዜም ፋሲካ ያደርግ ዘንድ ይገባል፤ እንደ ሀገር ልጅም ይሆንላችኋል፤ ያልተገረዘ ሁሉ ግን ከእርሱ አይብላ።
ዘፍጥረት 21:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አብርሃምም ልጁን ይስሐቅን እግዚአብሔር እንዳዘዘው በስምንተኛው ቀን ገረዘው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አብርሃም፣ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት ልጁን ይሥሐቅን በተወለደ በስምንተኛው ቀን ገረዘው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አብርሃምም ልጁን ይስሐቅን እግዚአብሔር እንዳዘዘው በስምንተኛ ቀን ገረዘው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይስሐቅ ከተወለደ ከስምንት ቀን በኋላ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት አብርሃም ገረዘው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አብርሃምም ልጁን ይስሐቅን እግዚአብሔር እንዳዘዘው በስምንተኛ ቀን ገረዘው። |
የእግዚአብሔርን ፋሲካ ያደርግ ዘንድ ወደ እናንተ የመጣ መጻተኛ ቢኖር ወንዱን ሁሉ ትገርዛለህ፤ ያን ጊዜም ፋሲካ ያደርግ ዘንድ ይገባል፤ እንደ ሀገር ልጅም ይሆንላችኋል፤ ያልተገረዘ ሁሉ ግን ከእርሱ አይብላ።
ስምንት ቀን በተፈጸመ ጊዜም ሕፃኑን ሊገዝሩት ወሰዱት፤ በማኅፀንዋ ሳትፀንሰው መልአኩ እንዳወጣለትም ስሙን ኢየሱስ አሉት።
የግዝረትንም ኪዳን ሰጠው፤ ከዚህም በኋላ ይስሐቅን ወለደ፤ በስምንተኛው ቀንም ገረዘው፤ እንዲሁ ይስሐቅም ያዕቆብን፥ ያዕቆብም ዐሥራ ሁለቱን የቀደሙ አባቶችን ገረዙ።