Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፍጥረት 21:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 አብ​ር​ሃ​ምም ሣራ የወ​ለ​ደ​ች​ለ​ትን የል​ጁን ስም ይስ​ሐቅ ብሎ ጠራው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 አብርሃም፣ ሣራ የወለደችለትን ልጅ ስሙን ይሥሐቅ አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 አብርሃምም የተወለደለትን ሣራ የወለደችለትን የልጁን ስም ይስሐቅ ብሎ ጠራው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 አብርሃም ሚስቱ ሣራ የወለደችለትን ልጅ “ይስሐቅ” ብሎ ስም አወጣለት፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 አብርሃምም የተወለደለትን ሣራ የወለደችለትን የልጁን ስም ይስሐቅ ብሎ ጠራው።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 21:3
11 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አብ​ር​ሃ​ምን አለው፥ “እሺ እነሆ፥ ሚስ​ትህ ሣራ ወንድ ልጅን ትወ​ል​ድ​ል​ሃ​ለች፤ ስሙ​ንም ይስ​ሐቅ ብለህ ትጠ​ራ​ዋ​ለህ፤ ለእ​ር​ሱና ከእ​ርሱ በኋላ ለዘሩ አም​ላክ እሆን ዘንድ ቃል ኪዳ​ኔን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ቃል ኪዳን ከእ​ርሱ ጋር አቆ​ማ​ለሁ።


ቃል ኪዳ​ኔን ግን በሚ​መ​ጣው ዓመት በዚሁ ጊዜ ሣራ ከም​ት​ወ​ል​ድ​ልህ ከይ​ስ​ሐቅ ጋር አቆ​ማ​ለሁ።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አብ​ር​ሃ​ምን አለው፥ “ስለ​ዚች አገ​ል​ጋ​ይ​ህና ስለ ሕፃኑ አት​ዘን፤ ሣራም የም​ት​ነ​ግ​ር​ህን ቃል ሁሉ ስማ፤ በይ​ስ​ሐቅ ዘር ይጠ​ራ​ል​ሃ​ልና።


ሣራም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደስ አሰ​ኘኝ፤ ይህን የሚ​ሰማ ሁሉ በእኔ ምክ​ን​ያት ደስ ይሰ​ኛ​ልና” አለች።


“የም​ት​ወ​ድ​ደ​ውን አንድ ልጅ​ህን ይስ​ሐ​ቅን ይዘህ ወደ ከፍ​ተ​ኛው ተራራ ሂድ፤ እኔም በም​ነ​ግ​ርህ በአ​ንድ ተራራ ላይ በዚያ መሥ​ዋ​ዕት አድ​ር​ገህ ሠዋው” አለው።


የአ​ብ​ር​ሃም ልጅ የይ​ስ​ሐቅ ትው​ል​ድም ይህ ነው፤ አብ​ር​ሃም ይስ​ሐ​ቅን ወለደ፥


አብርሃም ይስሐቅን ወለደ፤ ይስሐቅም ያዕቆብን ወለደ፤ ያዕቆብም ይሁዳንና ወንድሞቹን ወለደ፤


የግ​ዝ​ረ​ት​ንም ኪዳን ሰጠው፤ ከዚ​ህም በኋላ ይስ​ሐ​ቅን ወለደ፤ በስ​ም​ን​ተ​ኛው ቀንም ገረ​ዘው፤ እን​ዲሁ ይስ​ሐ​ቅም ያዕ​ቆ​ብን፥ ያዕ​ቆ​ብም ዐሥራ ሁለ​ቱን የቀ​ደሙ አባ​ቶ​ችን ገረዙ።


የአ​ብ​ር​ሃም ዘር ሁሉ ልጆቹ የሆ​ኑት አይ​ደ​ለም፤ ከይ​ስ​ሐቅ ዘር ይጠ​ራ​ል​ሃል አለው እንጂ።


“በይ​ስ​ሐቅ ዘር ይጠ​ራ​ል​ሃል” ብሎ ተስፋ ያና​ገ​ረ​ለ​ትን አንድ ልጁን አቀ​ረ​በው።


አባ​ታ​ች​ሁ​ንም አብ​ር​ሃ​ምን ከወ​ንዝ ማዶ ወስጄ በከ​ነ​ዓን ምድር ሁሉ መራ​ሁት፤ ዘሩ​ንም አበ​ዛሁ፤ ይስ​ሐ​ቅ​ንም ሰጠ​ሁት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos