ዘፍጥረት 20:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አብርሃምም ወደ እግዚዘብሔር ጸለየ፤ እግዚአብሔርም አቤሜሌክን፥ ሚስቱንም፥ ሴቶች ልጆቹንም፥ በቤቱ ውስጥ ያሉ ሴቶች አገልጋዮቹንም ፈወሳቸው፤ እነርሱም ወለዱ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም አብርሃም ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ እግዚአብሔርም አቢሜሌክን፣ ሚስቱንና ሴት አገልጋዮቹን ፈወሳቸው፤ እንደ ገናም ልጅ ለመውለድ በቍ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አብርሃምም ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፥ እግዚአብሔርም አቢሜሌክን ሚስቱንም ባርያዎቹንም ፈወሳቸው፥ እነርሱም ወለዱ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያ በኋላ አብርሃም ለእግዚአብሔር ጸለየ፤ እግዚአብሔርም አቤሜሌክንና ሚስቱን፥ ሴቶች አገልጋዮቹንም ፈውሶአቸው ልጆች እንዲወልዱ አድርጎአቸዋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አብርሃምም ወደ እግዚአብሔር ጸለየ እግዚአብሔርም አቢሜሌክን ሚስቱንም ባሪያዎቹንምም ፈውሳቸው |
አሁንም የሰውየውን ሚስት መልስ፤ ነቢይ ነውና፥ ስለ አንተም ይጸልያል፤ ትድናለህም። ባትመልሳት ግን አንተ እንድትሞት፥ ለአንተ የሆነውም ሁሉ እንዲሞት በርግጥ ዕወቅ።”
አሁን እንግዲህ ሰባት ወይፈኖችንና ሰባት አውራ በጎችን ይዛችሁ ወደ ባሪያዬ ወደ ኢዮብ ዘንድ ሂዱ፥ እርሱም የሚቃጠልን መሥዋዕት ስለ ራሳችሁ ያሳርግላችሁ። ባሪያዬም ኢዮብ ስለ እናንተ ይጸልይ፥ እኔም ፊቱን እቀበላለሁ። ስለ እርሱ ባይሆን ባጠፋኋችሁ ነበር። በባሪያዬ በኢዮብ ላይ ቅን ነገርን በፊቴ አልተናገራችሁምና።”
እግዚአብሔር ከኃጥኣን ፈጽሞ ይርቃል፤ የጻድቃንን ጸሎት ግን ይሰማል። ከዐመፃ ጋር ካለ ብዙ ሀብት ይልቅ፥ ከእውነት ጋር ያለ ጥቂት ሀብት ይሻላል። አካሄዱ ከእግዚአብሔር ይቃናለት ዘንድ፥ የደግ ሰው ልብ እውነትን ያስባል።
“የእስራኤልም ቅዱስ የሚመጣውንም የፈጠረ እግዚአብሔር አምላክ እንዲህ ይላል፦ ስለ ወንዶችና ሴቶች ልጆች ጠይቁኝ፤ ስለ እጄም ሥራ እዘዙኝ።
ሕዝቡም ወደ ሙሴ መጥተው፥ “በእግዚአብሔርና በአንተ ስለ ተናገርን በድለናል፤ እባቦችን ከእኛ ያርቅልን ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸልይልን” አሉት። ሙሴም ስለ ሕዝቡ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ።