ዘፍጥረት 20:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አብርሃምም አለ፥ “ምንአልባት በዚህ ስፍራ እግዚአብሔርን መፍራት ስለሌለ በሚስቴ ምክንያት ይገድሉኛል ብዬ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አብርሃምም አቢሜሌክን እንዲህ አለው፤ “ ‘እዚህ ቦታ ፈሪሀ እግዚአብሔር አለመኖሩን ተገነዘብሁ፤ ሰዎቹም ለሚስቴ ሲሉ ይገድሉኛል’ ብዬ ሠጋሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አብርሃምም አለ፦ “በዚህ ስፍራ እግዚአብሔርን መፍራት በእውነት እንደሌለ፥ ለሚስቴም ሲሉ እንደሚገድሉኝ ስላሰብሁ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አብርሃምም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ ‘እዚህ ቦታ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው የለም’ ብዬ በማሰብ ‘ሚስቴን ለመውሰድ በመፈለግ ይገድሉኛል’ ብዬ ስለ ሰጋሁ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አብርሃምም አለ፤ በዚህ ስፍራ እግዚአብሔርን መፍራት በእውነት እንድሌለ ለሚስቴም ሲሉ እንደሚገድሉኝ ስላሰብሁ ነው። |
እርሱም፥ “በብላቴናው ላይ እጅህን አትዘርጋ፤ አንዳችም አታድርግበት፤ ለምትውድደው ልጅህ ከእኔ አልራራህለትምና አንተ እግዚአብሔርን የምትፈራ እንደሆንህ አሁን ዐውቄአለሁ” አለው።
ከእኔ አስቀድመው የነበሩት አለቆች ግን በሕዝቡ ላይ አክብደው ነበር፤ ስለ እንጀራውና ስለ ወይኑ አርባ ሰቅል ብር ይወስዱ ነበር፤ ሎሌዎቻቸውም ደግሞ በሕዝቡ ላይ ይሰለጥኑ ነበር። እኔ ግን እግዚአብሔርን ስለ ፈራሁ እንዲህ አላደረግሁም።
አውስጢድ በሚባል ሀገር ስሙ ኢዮብ የተባለ አንድ ሰው ነበረ፤ ያም ሰው ቅን፥ ንጹሕና ጻድቅ፥ እግዚአብሔርንም የሚፈራ፥ ከክፉ ሥራም ሁሉ የራቀ ነበር።
የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ ዕውቀት ለሚያደርጋት ሁሉ መልካም ናት። እግዚአብሔርን መፍራት የዕውቀት መጀመሪያ ነው፥ ሰነፎች ግን ጥበብንና ተግሣጽን ይንቃሉ።