ዘፍጥረት 2:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር አምላክ ሰማይንና ምድርን በፈጠረበት ቀን፥ በተፈጠሩ ጊዜ የሰማይና የምድር ፍጥረት ይህ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር አምላክ ሰማያትንና ምድርን በፈጠረ ጊዜ የተከናወኑት እንደዚህ ነበረ፤ እግዚአብሔር አምላክ ሰማያትንና ምድርን ሲፈጥር፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ እግዚአብሔር ሰማያትንና ምድርን በፈጠረበት ቀን፥ የሰማያትና ምድር ልደት፥ በተፈጠሩበት ጊዜ፥ እንዲህ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሰማይና የምድር አፈጣጠር እንዲህ ነበር። እግዚአብሔር አምላክ ሰማይንና ምድርን በፈጠረ ጊዜ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር አምላክ ሰማይንና ምድርን ባደረገ አምላክ ሰማይንና ምድርን ቀን፤ በተፈጠሩ ጊዜ የሰማይና የምድር ልደት ይህ ነው። |
እግዚአብሔርም ባረካቸው፤ እንዲህም አላቸው፥ “ብዙ፤ ተባዙ፤ ምድርንም ሙሉአት፤ ግዙአትም፤ የባሕርን ዓሣዎችንና የምድር አራዊትን፥ የሰማይ ወፎችንና እንስሳትንም ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ግዙአቸው።”
ሕዝቡም ሁሉ ያን ባዩ ጊዜ በግንባራቸው ተደፍተው፥ “እግዚአብሔር በእውነት እርሱ አምላክ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ አምላክ ነው” አሉ።
እንዲህም አለ፥ “አቤቱ፥ የአባቶቻችን አምላክ ሆይ፥ በሰማይ ያለህ አምላክ አንተ አይደለህምን? የአሕዛብንስ መንግሥታት ሁሉ የምትገዛ አንተ አይደለህምን? ኀይልና ችሎታ በእጅህ ነው፤ ሊቋቋምህም የሚችል የለም።
እነዚህም እንደ ወገኖቻቸው የሌዊ ልጆች ስሞች ናቸው፤ ጌድሶን፥ ቀዓት፥ ሜራሪ ናቸው። የሌዊም የሕይወት ዘመን መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ነው።
የእስራኤል ንጉሥ እግዚአብሔር፥ የሚቤዥም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ እንዲህ ይላል፥ “እኔ ፊተኛ ነኝ፤ እኔም ኋለኛ ነኝ፤ ከእኔ ሌላም አምላክ የለም።
ዮሐንስ በእስያ ላሉት ለሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት፤ ካለውና ከነበረው፥ ከሚመጣውም፥ በዙፋኑም ፊት ካሉት ከሰባቱ መናፍስት፥ ከታመነውም ምስክር፥ ከሙታንም በኵር፥ የምድርም ነገሥታት ገዥ ከሆነ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። ለወደደን፥ ከኀጢአታችንም በደሙ ላጠበን፥
ለእግዚአብሔር እየሰገዱ እንዲህ አሉ “ያለህና የነበርህ ሁሉን የምትገዛ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! ትልቁን ኀይልህን ስለ ያዝህ ስለ ነገሥህም እናመሰግንሃለን፤