ዘፍጥረት 2:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም የሠራውን ሥራ በስድስተኛው ቀን ፈጸመ፤ እግዚአብሔርም በሰባተኛው ቀን ከሠራው ሥራ ሁሉ ዐረፈ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ይሠራ የነበረውን ሥራውን በሰባተኛው ቀን ላይ ፈጽሞ ነበር፤ ስለዚህ ይሠራ ከነበረው ሥራው ሁሉ በሰባተኛው ቀን ዐረፈ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔርም የሠራውን ሥራ በሰባተኛው ቀን ፈጸመ፥ በሰባተኛውም ቀን ከሠራው ሥራ ሁሉ ዐረፈ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሥራውን ሁሉ ፈጽሞ በሰባተኛው ቀን ዐረፈ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም የሠራውን ሥራ በሰባተኚው ቀን ፈጸመ፤ በሰባተኚውም ቀን ከሠራው ሥራ ሁሉ ዐረፈ። ፈጸመ፤ በሰባተኚውም ቀን ከሠራው ሥራ ሁሉ ዐረፈ። |
ስድስት ቀን ሥራህን ሁሉ ሥራ፤ በሬህና አህያህ ያርፉ ዘንድ ለባሪያህም ልጅ ለመጻተኛውም ዕረፍት ይሆን ዘንድ በሰባተኛው ቀን ዕረፍ።
ስድስት ቀን ሥራህን ሥራ፤ ሰባተኛዋ ቀን ግን ለእግዚአብሔር የተቀደስች የዕረፍት ሰንበት ናት፤ በሰንበት ቀን የሚሠራ ሁሉ ፈጽሞ ይገደል።
እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን በስድስት ቀን ስለ ፈጠረ፥ በሰባተኛውም ቀን ሥራውን ፈጽሞ ስላረፈ፥ በእኔና በእስራኤል ልጆች ዘንድ የዘለዓለም ምልክት ነው።”
ፈቃድህን በተቀደሰው ቀኔ ከማድረግ እግርህን ከሰንበት ብትመልስ፥ ሰንበትንም ደስታ፥ ለእግዚአብሔርም የተቀደሰ ብታደርገው፥ ክፉ ሥራን ለመሥራት እግርህን ባታነሣ፥ በአፍህም ክፉ ነገርን ባትናገር፥
ሰባተኛው ቀን ግን ለእግዚአብሔር ለአምላክህ ሰንበት ነው፤ አንተ እንደምታርፍ ሎሌህና ገረድህ ያርፉ ዘንድ፥ አንተ፥ ወንድ ልጅህም፥ ሴት ልጅህም፥ ሎሌህም፥ ገረድህም፥ በሬህም፥ አህያህም፥ ከብትህም ሁሉ፥ በደጆችህም ውስጥ ያለ መጻተኛ በእርሱ ምንም ሥራ አትሥሩ።