ዘፍጥረት 19:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም አላቸው፥ “ወንድሞች ሆይ፥ ለእናንተ አግባባችሁ አይደለም፤ በእነዚህ ላይ ክፉ አታድርጉ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህ አለ፤ “ወዳጆቼ ሆይ፤ እባካችሁ እንዲህ ያለውን ክፉ ነገር አታድርጉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም አለ፦ “ወንድሞቼ ሆይ፥ ይህን ክፉ ነገር አታድርጉ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲህም አላቸው “ወዳጆቼ ሆይ፥ እባካችሁ ይህን ክፉ ነገር አታድርጉ! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወንድሞቼ ሆይ፥ ይህን ክፉ ነገር አታድርጉ፤ |
እነሆ፥ ወንድን ያላወቁ ሁለት ሴቶች ልጆች አሉኝ፤ እነርሱን ላውጣላችሁ፤ እንደ ወደዳችሁም አድርጉአቸው፤ በእነዚህ ሰዎች ብቻ ምንም በደል አታድርጉ፤ እነርሱ በቤቴ ጥላ ሥር ገብተዋልና።”
ማናቸውም ሰው ከሴት ጋር እንደሚተኛ ከወንድ ጋር ቢተኛ ሁለቱ ጸያፍ ነገር አድርገዋል፤ ፈጽመው ይገደሉ፤ በደለኞች ናቸው።
እርሱም በምድር ሁሉ ላይ ይኖሩ ዘንድ ሰዎችን ሁሉ ከአንድ ሰው ፈጠረ፤ ይኖሩባትም ዘንድ ዘመንንና ቦታን ወስኖ ሠራላቸው።
እንዲሁም እንደ እነርሱ ዝሙትን ያደረጉና ሌላን ሥጋ የተከተሉ ሰዶምና ገሞራ በዙሪያቸውም የነበሩ ከተማዎች በዘላለም እሳት እየተቀጡ ምሳሌ ሆነዋል።
ባለቤቱም ሽማግሌው ወደ እነርሱ ወጥቶ፥ “ወንድሞቼ ሆይ! ይህን ክፉ ነገር ታደርጉ ዘንድ አይገባችሁም፤ ይህ ሰው ወደ ቤቴ ከገባ በኋላ እንደዚህ ያለ ስንፍና አትሥሩ።