ጎህም በቀደደ ጊዜ መላእክት ሎጥን፥ “ተነሣ፤ ሚስትህንና ከዚህ ያሉትን ሁለቱን ሴቶች ልጆችህን ውሰድ፤ አንተም በከተማዪቱ ሰዎች ኀጢአት እንዳትጠፋ” እያሉ ያስቸኩሉት ነበር።
ዘፍጥረት 19:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሎጥም ወጣ፤ ልጆቹን ለሚያገቡት ለአማቾቹም አላቸው፥ “ተነሡ፤ ከዚች ስፍራ ውጡ፤ እግዚአብሔር ይህችን ከተማ ያጠፋታልና።” ለአማቾቹ ግን የሚያፌዝባቸው መሰላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሎጥ ከቤቱ ወጥቶ የሴት ልጆቹ እጮኞች የሆኑትን ዐማቾቹን፣ “እግዚአብሔር ይህችን ከተማ ሊያጠፋት ነውና በፍጥነት ከዚህ ስፍራ ውጡ” አላቸው፤ ዐማቾቹ ግን የሚቀልድ መሰላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሎጥም ወጣ፥ ልጆቹን ለሚያገቡት ለአማቾቹም ነገራቸው፥ አላቸውም፦ ተነሡ፥ ከዚህ ስፍራ ውጡ፥ እግዚአብሔር ይህችን ከተማ ያጠፋልና። አማቾቹ ግን የሚያፌዝባቸው መሰላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ሎጥ ሴቶች ልጆቹን ወዳጩአቸው ሰዎች ቤት ሄደና “ቶሎ ብላችሁ ከዚህ ውጡ፤ እግዚአብሔር ይህን ስፍራ ሊደመስሰው ነው” አላቸው፤ እነርሱ ግን የሚቀልድ መስሎአቸው ቸል አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሎጥ፥ ወጣ ልጆቹም ለሚያገቡት ለአማቶቹም ነገራቸው አላቸውም፥ ተነሡ ከዚህ ስፍራ ውጡ እግዚአብሔር ይህችን ከተማ ያጠፋልና። ለአማቶቹ ግን የሚያፌዝባቸው መሰላቸው |
ጎህም በቀደደ ጊዜ መላእክት ሎጥን፥ “ተነሣ፤ ሚስትህንና ከዚህ ያሉትን ሁለቱን ሴቶች ልጆችህን ውሰድ፤ አንተም በከተማዪቱ ሰዎች ኀጢአት እንዳትጠፋ” እያሉ ያስቸኩሉት ነበር።
ወደ ሜዳም በወጡ ጊዜ እንዲህ አሉት፥ “ራስህን አድን፤ ወደ ኋላም አትመልከት፤ አንተንም መከራ እንዳታገኝህ በዚች ሀገር በዳርቻዋና በተራራዋ አትቁም።”
እንግዲህ ፍጠንና በዚያ ራስህን አድን፤ ወደዚያ እስክትደርስ ድረስ ምንም አደርግ ዘንድ አልችልምና።” ስለዚህም የዚያች ከተማ ስም ሴጎር ተባለ።
መልእክተኞቹም ከከተማ ወደ ከተማ በኤፍሬምና በምናሴ ሀገር እስከ ዛብሎን ሄዱ፤ እነዚያ ግን በንቀት ሳቁባቸው፤ አፌዙባቸውም።
እነርሱ ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በሕዝቡ ላይ እስኪወጣ ድረስ፥ ፈውስም እስከማይገኝላቸው ድረስ፥ በእግዚአብሔር መልእክተኞች ይሳለቁ፥ ቃሉንም ያቃልሉ፥ በነቢያቱም ላይ ያፌዙ ነበር።
ፈርዖንም ሙሴንና አሮንን በሌሊት ጠርቶ አላቸው፥ “እናንተ የእስራኤልም ልጆች ተነሡ፤ ከሕዝቤ መካከል ውጡ፤ ሂዱም፤ እንዳላችሁም እግዚአብሔርን አምልኩት፤
አሁንም በምድር ሁሉ ላይ የሚያደርገውን ያለቀና የተቈረጠ ነገርን ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ዘንድ ሰምቻለሁና እስራታችሁ እንዳይጸናባችሁ እናንተ ደስ አይበላችሁ።
የአምላካቸውን የእግዚአብሔርን ቃል ሁሉ፥ ለእነርሱ አምላካቸው እግዚአብሔር የላከውን ይህን ቃል ሁሉ፥ ኤርምያስ ለሕዝቡ ሁሉ መናገርን በፈጸመ ጊዜ እንዲህ ሆነ፤
የኢዮስያስ ልጅ ኣዛርያስ፥ የቃርሔም ልጅ ዮሐናን፥ ትዕቢተኞችም ሰዎች ሁሉ ኤርምያስን፥ “ሐሰት ተናግረሃል፤ አምላካችን እግዚአብሔር፦ በዚያ ትቀመጡ ዘንድ ወደ ግብፅ አትግቡ ብሎ አልላከህም፤
ከባቢሎን መካከል ሽሹ፤ እያንዳንዳችሁም ነፍሳችሁን አድኑ፤ በበደልዋ አትጥፉ፤ የእግዚአብሔር በቀል ጊዜ ነውና፥ እርሱም ብድራቷን ይከፍላታልና።
ማኅበሩንም፥ “ከእነዚህ ክፉዎች ሰዎች ድንኳን ፈቀቅ በሉ፤ በኀጢአታቸውም ሁሉ እንዳትጠፉ ለእነርሱ የሆነውን ሁሉ አትንኩ” ብሎ ተናገራቸው።
ሲያመጣውም ጋኔኑ ጣለውና አፈራገጠው፤ ጌታችን ኢየሱስም ያን ክፉ ጋኔን ገሠጸው፤ ልጁንም አዳነው፤ ለአባቱም ሰጠው። ሁሉም ከእግዚአብሔር ታላቅነት የተነሣ አደነቁ።