Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤርምያስ 43:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 የአ​ም​ላ​ካ​ቸ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ሁሉ፥ ለእ​ነ​ርሱ አም​ላ​ካ​ቸው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የላ​ከ​ውን ይህን ቃል ሁሉ፥ ኤር​ም​ያስ ለሕ​ዝቡ ሁሉ መና​ገ​ርን በፈ​ጸመ ጊዜ እን​ዲህ ሆነ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ኤርምያስ፣ እግዚአብሔር ለእነርሱ እንዲነግራቸው የላከውን የአምላካቸውን የእግዚአብሔርን ቃል ሁሉ ለሕዝቡ ተናግሮ በጨረሰ ጊዜ፣

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ለእነርሱ አምላካቸው እግዚአብሔር የላከውን ይህን የአምላካቸውን የጌታን ቃል ሁሉ፥ ኤርምያስ ለሕዝቡ ሁሉ መናገርን በፈጸመ ጊዜ፥

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 አምላካቸው እግዚአብሔር እንድነግራቸው ያዘዘኝን ሁሉ ለሕዝቡ ተናግሬ ፈጸምኩ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 የአምላካቸውን የእግዚአብሔርን ቃል ሁሉ፥ ለእነርሱ አምላካቸው እግዚአብሔር የላከውን ይህን ቃል ሁሉ፥ ኤርምያስ ለሕዝቡ ሁሉ መናገርን በፈጸመ ጊዜ፥

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 43:1
15 Referencias Cruzadas  

ሎጥም ወጣ፤ ልጆ​ቹን ለሚ​ያ​ገ​ቡት ለአ​ማ​ቾ​ቹም አላ​ቸው፥ “ተነሡ፤ ከዚች ስፍራ ውጡ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህ​ችን ከተማ ያጠ​ፋ​ታ​ልና።” ለአ​ማ​ቾቹ ግን የሚ​ያ​ፌ​ዝ​ባ​ቸው መሰ​ላ​ቸው።


ሙሴም ገባ፤ ለሕ​ዝ​ቡም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃሎች ሁሉ፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንም ሁሉ ነገረ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ በአ​ንድ ድምፅ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ና​ገ​ራ​ቸ​ውን ቃሎች ሁሉ እን​ሰ​ማ​ለን፤ እና​ደ​ር​ጋ​ለ​ንም” ብለው መለሱ።


አንተ ግን ወገ​ብ​ህን ታጠቅ፤ ተነ​ሥም፤ ያዘ​ዝ​ሁ​ህ​ንም ሁሉ ንገ​ራ​ቸው፤ ከፊ​ታ​ቸ​ውም የተ​ነሣ አት​ፍራ። በፊ​ታ​ቸ​ውም አት​ደ​ን​ግጥ አድ​ንህ ዘንድ እኔ ከአ​ንተ ጋር ነኝና ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን እን​ዲህ አለኝ፥ “ወደ​ም​ል​ክህ ሁሉ ዘንድ ትሄ​ዳ​ለ​ህና፥ የማ​ዝ​ዝ​ህ​ንም ሁሉ ትና​ገ​ራ​ለ​ህና፦ ሕፃን ነኝ አት​በል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አደ​ባ​ባይ ቁም፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ውስጥ ይሰ​ግዱ ዘንድ ለሚ​መ​ጡት ለይ​ሁዳ ከተ​ሞች ሁሉ ትነ​ግ​ራ​ቸው ዘንድ ያዘ​ዝ​ሁ​ህን ቃል ሁሉ ተና​ገ​ራ​ቸው፤ አን​ዲ​ትም ቃል አታ​ጕ​ድል።


ኤር​ም​ያ​ስም ለሕ​ዝቡ ሁሉ ይና​ገር ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዘ​ውን ነገር ሁሉ በፈ​ጸመ ጊዜ ካህ​ና​ትና ነቢ​ያተ ሐሰት፥ ሕዝ​ቡም ሁሉ፥ “ሞትን ትሞ​ታ​ለህ” ብለው ያዙት።


እኔም ዛሬ ነግ​ሬ​አ​ች​ኋ​ለሁ፤ ወደ እና​ን​ተም በላ​ከኝ ነገር ሁሉ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል አል​ሰ​ማ​ች​ሁም።


አሁ​ንም ሄዳ​ችሁ እን​ድ​ት​ቀ​መጡ በወ​ደ​ዳ​ች​ሁ​በት ስፍራ በሰ​ይ​ፍና በራብ፥ በቸ​ነ​ፈ​ርም እን​ድ​ት​ሞቱ በእ​ር​ግጥ ዕወቁ።”


የይ​ሁ​ዳም ወገ​ኖች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዋሹ፤ እን​ዲ​ህም አሉ፥ “እን​ደ​ዚህ አይ​ደ​ለም፤ ክፉ ነገ​ርም አይ​መ​ጣ​ብ​ንም ሰይ​ፍ​ንና ራብ​ንም አና​ይም፤


ይህ​ንም መጽ​ሐፍ ማን​በብ ከፈ​ጸ​ምህ በኋላ፥ ድን​ጋ​ይን እሰ​ር​በት፤ በኤ​ፍ​ራ​ጥ​ስም ወንዝ ውስጥ ጣለው።


ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምክር ሁሉ የሰ​ወ​ር​ኋ​ች​ሁና ያል​ነ​ገ​ር​ኋ​ችሁ የለም።


“ሂዱ፤ ወደ ቤተ መቅ​ደ​ስም ግቡና ለሕ​ዝብ ይህን የሕ​ይ​ወት ቃል አስ​ተ​ም​ሩ​አ​ቸው።”


ሳሙ​ኤ​ልም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ሁሉ ንጉ​ሥን ለፈ​ለጉ ሕዝብ ነገ​ራ​ቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos