አብርሃምም ከዚያ ተነሥቶ ወደ አዜብ ምድር አቅጣጫ ሄደ፤ በቃዴስና በሱር መካከልም ኖረ፤ በጌራራም በእንግድነት ተቀመጠ።
ዘፍጥረት 16:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔር መልአክም በውኃ ምንጭ አጠገብ በሱር በረሃ በመንገድ አገኛት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔር መልአክ አጋርን በአንድ የውሃ ምንጭ አጠገብ በምድረ በዳ አገኛት፤ ምንጩም ወደ ሱር በሚወስደው መንገድ ዳር ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእግዚአብሔር መልአክም በውኃ ምንጭ አጠገብ በበረሀ አገኛት፥ ምንጩም ወደ ሱር በምትወስደው መንገድ አጠገብ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእግዚአብሔር መልአክ አጋርን በበረሓ በሚገኘው በአንድ ምንጭ አጠገብ አገኛት፤ ይህም ምንጭ ወደ ሹር በሚወስደው መንገድ ላይ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔር መልአክም በውኃ ምንጭ አጠገብ በበረሀ አገኛት፤ ምንጩም ወደ ሱር በምትወስደው መንገድ አጠገብ ነው። |
አብርሃምም ከዚያ ተነሥቶ ወደ አዜብ ምድር አቅጣጫ ሄደ፤ በቃዴስና በሱር መካከልም ኖረ፤ በጌራራም በእንግድነት ተቀመጠ።
እግዚአብሔርም የሕፃኑን ጩኸት ሰማ፤ የእግዚአብሔርም መልአክ ከሰማይ አጋርን እንዲህ ሲል ጠራት፥ “አጋር ሆይ፥ ምን ሆንሽ? እግዚአብሔር የልጅሽን ድምፅ ባለበት ስፍራ ሰምቶአልና አትፍሪ።
እግዚአብሔርም ለአጋር ዐይንዋን ከፈተላት፤ የውኃ ጕድጓድንም አየች፤ ሄዳም አቍማዳውን በውኃ ሞላች፤ ልጅዋንም አጠጣችው።
ከአባቴ ቤት፥ ከተወለድሁባት ምድር ያወጣኝ፦ ‘ይህችንም ምድር ለአንተና ለዘርህ እሰጥሃለሁ’ ብሎ የነገረኝና የማለልኝ የሰማይና የምድር አምላክ እግዚአብሔር፥ እርሱ መልአኩን በፊትህ ይሰድዳል፤ ከዚያም ለልጄ ሚስትን ትወስዳለህ።
ሙሴም የእስራኤልን ልጆች ከኤርትራ ባሕር አውጥቶ ወደ ሱር ምድረ በዳ ወሰዳቸው። በምድረ በዳም ሦስት ቀን ተጓዙ፤ ይጠጡም ዘንድ ውኃ አላገኙም።
የእግዚአብሔርም መልአክ ለሙሴ በእሳት ነበልባል በቍጥቋጦ መካከል ታየው፤ እነሆም፥ ቍጥቋጦው በእሳት ሲነድድ፥ ቍጥቋጦውም ሳይቃጠል አየ።