እንዲሁም እነዚህን ሁሉ ወሰደለት፤ በየሁለትም ከፈላቸው፤ የተከፈሉትንም በየወገኑ ትይዩ አደረጋቸው፤ ወፎችን ግን አልቈረጣቸውም።
ዘፍጥረት 15:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም አለው፥ “የሦስት ዓመት ላም፥ የሦስት ዓመት ፍየልም፥ የሦስት ዓመት በግም፥ ዋኖስም፥ ርግብም አምጣ፤ እኒህንም ሁሉ አምጥተህ ከሁለት ከሁለት ቍረጣቸው፤ ወፎችን ግን አትቍረጣቸው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም “እያንዳንዳቸው ሦስት ዓመት የሆናቸው አንዲት ጊደር፣ አንድ ፍየልና አንድ በግ፣ በተጨማሪም አንድ ዋኖስና አንድ ርግብ ዐብረህ አቅርብልኝ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም፦ የሦስት ዓመት ጊደር፥ የሦስት ዓመት ፍየልም፥ የሦስት ዓመት በግም፥ ዋኖስም፥ ርግብም ያዝልኝ አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም “ሦስት፥ ሦስት ዓመት የሆናቸው አንድ ጊደር፥ አንድ ፍየልና፥ አንድ በግ፥ እንዲሁም ዋኖስና ርግብ አምጣልኝ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም፥ የሦስት ዓመት ጊደር፥ የሦስት ዓመት ፍየልም፥ የሦስት በግም ዋኖስም ርግብም ያዝልኝ አለው። |
እንዲሁም እነዚህን ሁሉ ወሰደለት፤ በየሁለትም ከፈላቸው፤ የተከፈሉትንም በየወገኑ ትይዩ አደረጋቸው፤ ወፎችን ግን አልቈረጣቸውም።
አብርሃምም ዐይኖቹን አቅንቶ በተመለከተ ጊዜ፥ በኋላው እነሆ፥ አንድ በግ ቀንዶቹ በዕፀ ሳቤቅ ተይዞ አየ፤ አብርሃምም ሄዶ በጉን ወሰደው፤ በልጁ በይስሐቅ ፈንታም ሠዋው።
ሞዓብ ራሷን ይዛ ትጮኻለች፤ ለልቧም ይረዳታል፤ እስከ ሴጎርም ድረስ ብቻዋን ታለቅሳለች። ሞዓብ እንደ ሦስት ዓመት ጥጃ ናትና በሉሒት ዐቀበት ትጮኻለች። በአሮሜዎን መንገድም ይመለሳሉ፤ ይጮኻሉም፥ ጥፋትና መናወጥም ይሆናል።
“ነገር ግን ለእግዚአብሔር የሚቀርበው መባ ከበጎች ወይም ከፍየሎች ቢሆን፥ ለሚቃጠል መሥዋዕት ነውር የሌለበትን ተባቱን፥ የፊት እግሮቹንና ራሱን ጨምሮ ያቀርበዋል።
“ለእግዚአብሔርም የሚያቀርበው ቍርባን የሚቃጠል መሥዋዕት ከዎፎች ቢሆን፥ ቍርባኑን ከዋኖስ ወይም ከርግብ ያቀርባል።
“መባውም የሚቃጠል መሥዋዕት ከላሞች መንጋ ቢሆን፥ ነውር የሌለበትን ተባቱን ያቀርባል፤ በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት እንዲኖረው በምስክሩ ድንኳን ደጃፍ ፊት ያቀርበዋል።
“የመንጻቷ ወራትም በተፈጸመ ጊዜ፥ ለወንድ ልጅ ወይም ለሴት ልጅ፥ የአንድ ዓመት ጠቦት ለሚቃጠል መሥዋዕት፥ የርግብም ግልገል ወይም ዋኖስ ለኀጢአት መሥዋዕት ወደ ምስክሩ ድንኳን ደጃፍ ወደ ካህኑ ታመጣለች።
ጠቦት ለማምጣት የሚበቃ ገንዘብ በእጅዋ ባይኖራት ሁለት ዋኖሶች፥ ወይም ሁለት የርግብ ግልገሎች፥ አንዱን ለሚቃጠል መሥዋዕት፥ ሌላውንም ለኀጢአት መሥዋዕት ታቀርባለች፤ ካህኑም ያስተሰርይላታል፤ እርስዋም ትነጻለች።”
ሁለት ዋኖሶች፥ ወይም ሁለት የርግብ ግልገሎች በእጁ እንዳገኘ አንዲቱን ለኀጢአት መሥዋዕት፥ አንዲቱንም ለሚቃጠል መሥዋዕት ይወስዳል።
“ለእግዚአብሔር የሚቀርበው ቍርባን የደኅንነት መሥዋዕት ቢሆን፥ ከላሞች መንጋ ተባት ወይም እንስት ቢያቀርብ፥ ነውር የሌለበትን በእግዚአብሔር ፊት ያቅርብ።
“ለእግዚአብሔርም ለደኅንነት መሥዋዕት የሚያቀርበው ቍርባኑ ከበጎች ተባት ወይም እንስት ቢሆን፥ ነውር የሌለበትን ያቀርባል።
ሙሴም አሮንን አለው፥ “ስለ ኀጢአት መሥዋዕት ከመንጋው እንቦሳውን፥ ስለሚቃጠልም መሥዋዕት አውራውን በግ ወስደህ በእግዚአብሔር ፊት አቅርባቸው።
ለደኅንነትም መሥዋዕት በሬንና አውራ በግን፥ በዘይትም የተለወሰ የእህልን ቍርባን በእግዚአብሔር ፊት ይሠዉ ዘንድ ውሰዱ፤ ዛሬ እግዚአብሔር ይገለጥላችኋልና ብለህ ንገራቸው።”
በእግዚአብሔርም ሕግ እንደ ታዘዘ ሁለት ዋኖስ ወይም ሁለት የርግብ ግልገሎች ስለ እርሱ መሥዋዕት አድርገው ያቀርቡለት ዘንድ።