Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘሌዋውያን 12:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 “የመ​ን​ጻቷ ወራ​ትም በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ፥ ለወ​ንድ ልጅ ወይም ለሴት ልጅ፥ የአ​ንድ ዓመት ጠቦት ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት፥ የር​ግ​ብም ግል​ገል ወይም ዋኖስ ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ወደ ካህኑ ታመ​ጣ​ለች።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 “ ‘ሴትዮዋ ወንድ ወይም ሴት ልጅዋን ወልዳ የመንጻቷ ጊዜ ሲፈጸም፣ ለሚቃጠል መሥዋዕት የአንድ ዓመት ጠቦት፣ ለኀጢአት መሥዋዕት አንድ የዋኖስ ጫጩት ወይም አንድ ርግብ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ወስዳ ካህኑ ዘንድ ታቅርብ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 “የመንጻትዋ ወራትም በተፈጸመ ጊዜ፥ ለወንድ ልጅ ወይም ለሴት ልጅ፥ የአንድ ዓመት ጠቦት ለሚቃጠል መሥዋዕት፥ የርግብም ግልገል ወይም ዋኖስ ለኃጢአት መሥዋዕት ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ወደ ካህኑ ታምጣ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 “የመንጻትዋም ወራት በተፈጸመ ጊዜ ስለ ወንድ ልጅም ሆነ ስለ ሴት ልጅ የሚቃጠል መሥዋዕት ሆኖ የሚቀርብ የአንድ ዓመት የበግ ጠቦትና ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት የሚሆን ርግብ ወይም ዋኖስ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ አምጥታ በዚያ ለሚያገለግለው ካህን ትስጠው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 የመንጻትዋ ወራትም በተፈጸመ ጊዜ፥ ለወንድ ልጅ ወይም ለሴት ልጅ፥ የአንድ ዓመት ጠቦት ለሚቃጠል መሥዋዕት፥ የርግብም ግልገል ወይም ዋኖስ ለኃጢአት መሥዋዕት ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ወደ ካህኑ ታምጣለት።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 12:6
15 Referencias Cruzadas  

የመ​ን​ጻ​ታ​ቸ​ውም ወራት በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ እንደ ሙሴ ሕግ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያቆ​ሙት ዘንድ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወሰ​ዱት።


ቅዱ​ስና ያለ ተን​ኰል፥ ነው​ርም የሌ​ለ​በት፥ ከኀ​ጢ​አ​ተ​ኞ​ችም የተ​ለየ፥ ከሰ​ማ​ያ​ትም ከፍ ከፍ ያለ፥ እን​ደ​ዚህ ያለ ሊቀ ካህ​ናት ይገ​ባ​ናል።


ኀጢ​አት የሌ​ለ​በት እርሱ እኛን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያጸ​ድ​ቀን ዘንድ ስለ እኛ ራሱን እንደ ኃጥእ አድ​ር​ጓ​ልና።


በማ​ግ​ሥ​ቱም ዮሐ​ንስ ወደ እርሱ ሲመጣ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን አይቶ እን​ዲህ አለ፤ “እነሆ፥ የዓ​ለ​ሙን ኀጢ​ኣት የሚ​ያ​ስ​ወ​ግድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በግ።


በስ​ም​ን​ተ​ኛ​ውም ቀን ሁለት ዋኖ​ሶች ወይም ሁለት የር​ግብ ግል​ገ​ሎች ይዛ ወደ ካህኑ ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ታመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለች።


በስ​ም​ን​ተ​ኛ​ውም ቀን ሁለት ዋኖ​ሶች ወይም ሁለት የር​ግብ ግል​ገ​ሎች ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ወደ ካህኑ ያምጣ፤


በስ​ም​ን​ተ​ኛ​ውም ቀን ሁለት ዋኖ​ሶች ወይም ሁለት የር​ግብ ግል​ገ​ሎች ይዞ ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያመ​ጣል፤ ለካ​ህ​ኑም ይሰ​ጠ​ዋል።


ሁለት ዋኖ​ሶች፥ ወይም ሁለት የር​ግብ ግል​ገ​ሎች በእጁ እን​ዳ​ገኘ አን​ዲ​ቱን ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት፥ አን​ዲ​ቱ​ንም ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ይወ​ስ​ዳል።


“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ተና​ገ​ራ​ቸው፦ ሴት ብታ​ረ​ግዝ ወንድ ልጅም ብት​ወ​ልድ፥ ሰባት ቀን ያህል የረ​ከ​ሰች ናት፤


እር​ሱም አለው፥ “የሦ​ስት ዓመት ላም፥ የሦ​ስት ዓመት ፍየ​ልም፥ የሦ​ስት ዓመት በግም፥ ዋኖ​ስም፥ ርግ​ብም አምጣ፤ እኒ​ህ​ንም ሁሉ አም​ጥ​ተህ ከሁ​ለት ከሁ​ለት ቍረ​ጣ​ቸው፤ ወፎ​ችን ግን አት​ቍ​ረ​ጣ​ቸው።”


ሴት ልጅም ብት​ወ​ልድ እንደ ግዳ​ጅዋ ወራት ሁለት ሳም​ንት ያህል የረ​ከ​ሰች ናት፤ ከደ​ም​ዋም እስ​ክ​ት​ነጻ ድረስ ስድሳ ስድ​ስት ቀን ትቈይ።


ካህ​ኑም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያቀ​ር​በ​ዋል፤ ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ላ​ት​ማል፤ ከደ​ም​ዋም ፈሳሽ ትነ​ጻ​ለች። ወንድ ወይም ሴት ለም​ት​ወ​ልድ ሴት ሕጉ ይህ ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios