የከነዓናውያንም ወሰን ከሲዶን እስከ ጌራራና ጋዛ ድረስ ነው፤ ወደ ሰዶምና ወደ ገሞራ፥ ወደ አዳማና ወደ ሴባዮም እስከ ላሳ ይደርሳል።
ዘፍጥረት 14:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሰዶም ንጉሥ ከባላ፥ ከገሞራ ንጉሥ ከበርሳ፥ ከአዳማ ንጉሥ ከሰናአር፥ ከሲባዮ ንጉሥ ከሲምቦር፤ ሴጎር ከተባለች ከባላ ንጉሥም ጋር ጦርነት አደረጉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሰዶም ንጉሥ ከበላ፣ ከገሞራ ንጉሥ ከብርሳ፣ ከአዳማ ንጉሥ ከሰነአብ፣ ከስቦይ ንጉሥ ከሰሜበር፣ እንዲሁም ዞዓር ከተባለች ከቤላ ንጉሥ ጋራ ለመዋጋት ወጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሰዶም ንጉሥ ከባላ፥ ከገሞራ ንጉሥ ከብርሳ፥ ከአዳማ ንጉሥ ከሰነአብ፥ ከሰቦይም ንጉሥ ከሰሜበር፥ ዞዓር ከተባለች ከቤላ ንጉሥም ጋር ሰልፍ አደረጉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነዚህ አራቱ ነገሥታት፥ ሌሎችን አምስት ነገሥታት ለመውጋት ሄዱ፤ የተዘመተባቸውም አምስት ነገሥታት የሰዶም ንጉሥ ቤራዕ፥ የገሞራ ንጉሥ ቢርሻዕ፥ የአዳማ ንጉሥ ሺንአብ፥ የጸቦይም ንጉሥ ሼሜቤርና ጾዓር ተብላ የምትጠራው የቤላዕ ንጉሥ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህ ሆነ ከሰዶም ንጉሥ ከባላ፥ ከገሞራ ንጉሥ ከብርሳ፥ ከአዳማ ንጉሥ ከሰሜበር፥ ዞዓር ከተባለች ከቤላ ንግሥም ጋር ሰልፍ አደረጉ። |
የከነዓናውያንም ወሰን ከሲዶን እስከ ጌራራና ጋዛ ድረስ ነው፤ ወደ ሰዶምና ወደ ገሞራ፥ ወደ አዳማና ወደ ሴባዮም እስከ ላሳ ይደርሳል።
ሎጥም ዓይኖቹን አነሣ፤ በዮርዳኖስ ዙሪያ ያለውንም ሀገር ሁሉ ውኃ የሞላበት መሆኑን አየ፤ እግዚአብሔር ሰዶምንና ገሞራን ከማጥፋቱ አስቀድሞ እስከ ሴጎር ድረስ እንደ እግዚአብሔር ገነትና እንደ ግብፅ ምድር እንደ ነበረ አየ።
ሞዓብ ራሷን ይዛ ትጮኻለች፤ ለልቧም ይረዳታል፤ እስከ ሴጎርም ድረስ ብቻዋን ታለቅሳለች። ሞዓብ እንደ ሦስት ዓመት ጥጃ ናትና በሉሒት ዐቀበት ትጮኻለች። በአሮሜዎን መንገድም ይመለሳሉ፤ ይጮኻሉም፥ ጥፋትና መናወጥም ይሆናል።
ከሐሴቦን ጩኸት እስከ ኤሊያሊና እስከ ኢያሳ ድረስ ድምፃቸውን ሰጥተዋል፤ ከሴጎር እስከ ሖሮናይምና እስከ ዔግላት ሺሊሺያ ድረስ ይደርሳል፤ የኔምሬም ውኃ ደርቋልና።
እኔም “አምልኮቴን ትተሃል አልሁ፤ ኤፍሬም ሆይ! እንዴት አደርግሃለሁ? እስራኤል ሆይ! እንዴትስ እደግፍሃለሁ? እንዴትስ አደርግሃለሁ? እንደ አዳማ ነውን? ወይስ እንደ ሲባዮ? ልቤ በውስጤ ተናውጣለች፤ ምሕረቴም ተገልጣለች።
ምድርም በሁለንተናዋ ዲንና ጨው፥ መቃጠልም እንደ ሆነባት፥ እንዳይዘራባትም፥ እንዳታበቅልም፥ ማናቸውም ሣርና ልምላሜም እንዳይወጣባት፥ እግዚአብሔር በቍጣውና በመዓቱ እንደ ገለበጣቸው እንደ ሰዶምና ገሞራ፥ እንደ አዳማና እንደ ሲባዮ እንደ ሆነች ባዩ ጊዜ፥
ሁለተኛው ክፍል ወደ ቤቶሮን መንገድ ዞረ፤ ሦስተኛውም ክፍል በገባዖን መንገድ ባለው ወደ ሴቤሮም ሸለቆ በሚመለከተው በዳርቻው መንገድ ዞረ።