ለዔቦርም ሁለት ልጆች ተወለዱለት፤ የአንደኛው ስሙ ፋሌቅ ነው፤ ምድር በዘመኑ ተከፍላለችና፤ የወንድሙም ስም ዮቅጣን ነው።
ዘፍጥረት 11:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ቋንቋቸውን ለያየ፤ ከዚያም በምድር ፊት ሁሉ ላይ በተናቸው፤ ከዚያም በኋላ ከተማዪቱንና ግንቡን መሥራትን ተዉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ እግዚአብሔር በምድር ሁሉ ላይ በታተናቸው፤ ከተማዋንም መሥራት አቆሙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያ በኋላ ጌታ በምድር ሁሉ ላይ በተናቸው፥ ከተማይቱንም መሥራት አቆሙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር በምድር ሁሉ ላይ በተናቸው፤ ከተማውንም መሥራት አቆሙ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ከዚያ በምድር ሁሉ ላይ በተናቸው፤ ከተማይቱንም መሥራት ተው። |
ለዔቦርም ሁለት ልጆች ተወለዱለት፤ የአንደኛው ስሙ ፋሌቅ ነው፤ ምድር በዘመኑ ተከፍላለችና፤ የወንድሙም ስም ዮቅጣን ነው።
የኖኅ የልጆቹ ነገዶች እንደ ትውልዳቸው በየሕዝባቸው እነዚህ ናቸው። ከእነዚህም ከጥፋት ውኃ በኋላ ሕዝቦች በምድር ላይ ተዘሩ።
እርስ በርሳቸውም፥ “ኑ ለእኛ ከተማና ራሱ ወደ ሰማይ የሚደርስ ግንብ እንሥራ፤ በምድር ፊት ሁሉ ላይ ሳንበተን ስማችንን እናስጠራው” ተባባሉ።
ስለዚህም ስምዋ ባቢሎን ተባለ፤ እግዚአብሔር በዚያ የምድርን ቋንቋ ሁሉ ደባልቆአልና፤ ከዚያም እግዚአብሔር በምድር ሁሉ ፊት ላይ እነርሱን በትኖአቸዋል።
ቍጣቸው ርጉም ይሁን፤ ጽኑ ነበርና፤ ኵርፍታቸውም ብርቱ ነበርና፤ በያዕቆብ እከፋፍላቸዋለሁ፤ በእስራኤልም እበታትናቸዋለሁ።
ልዑል አሕዛብን በከፈላቸው ጊዜ፥ የአዳምንም ልጆች በለያቸው ጊዜ፥ እንደ እግዚአብሔር መላእክት ቍጥር፥ አሕዛብን በየድንበራቸው አቆማቸው።