እግዚአብሔርም አለ፥ “ሰውን በአርኣያችንና በአምሳላችን እንፍጠር፤ የባሕር ዓሣዎችንና የምድር አራዊትን፥ የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድርም ላይ የሚንቀሳቀሱትን ሁሉ ይግዛ።”
ዘፍጥረት 11:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኑ እንውረድ፤ አንዱ የሌላውን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚያ እንደባልቀው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኑ እንውረድ፤ እርስ በርሳቸውም እንዳይግባቡ ቋንቋቸውን እንደበላልቀው።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ኑ! እንውረድ፥ እርስ በርሳቸው እንዳይግባቡ ቋንቋቸውን እንደበላልቀው።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ኑ! እንውረድና እርስ በርሳቸው እንዳይግባቡ ቋንቋቸውን እንደበላልቀው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኑ፥ እንውረድ፤ እንውረድ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚይ እንደባልቀው። |
እግዚአብሔርም አለ፥ “ሰውን በአርኣያችንና በአምሳላችን እንፍጠር፤ የባሕር ዓሣዎችንና የምድር አራዊትን፥ የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድርም ላይ የሚንቀሳቀሱትን ሁሉ ይግዛ።”
የኖኅ የልጆቹ ነገዶች እንደ ትውልዳቸው በየሕዝባቸው እነዚህ ናቸው። ከእነዚህም ከጥፋት ውኃ በኋላ ሕዝቦች በምድር ላይ ተዘሩ።
እግዚአብሔር አምላክም አለ፥ “እነሆ፥ አዳም መልካምንና ክፉን ለማወቅ ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ፤ አሁንም እጁን እንዳይዘረጋ፥ ደግሞም ከሕይወት ዛፍ ወስዶ እንዳይበላ፥ ለዘለዓለምም ሕያው ሆኖ እንዳይኖር፥”
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “ለሰው አፍን የሰጠ ማን ነው? ዲዳስ፥ ደንቆሮስ፥ የሚያይስ፥ ዕውርስ የሚያደርግ ማን ነው? እኔ እግዚአብሔር አይደለሁምን?
የማታውቋቸውን አሕዛብ አመጣባችኋለሁ፤ እናንት ዐማፅያን ሕዝብ፥ ጥልቅ ነገርን ትሰማላችሁ። የሚሰማም ማስተዋል እንደሌለው ይሆናል።
የጌታንም ድምፅ፥ “ማንን እልካለሁ? ማንስ ወደዚያ ሕዝብ ይሄድልናል?” ሲል ሰማሁ? እኔም፥ “እነሆኝ፥ ጌታዬ፥ እኔን ላከኝ” አልሁ።
የእስራኤል ቤት ሆይ! እነሆ ሕዝብን ከሩቅ አመጣባችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ኀያል ጥንታዊ ሕዝብ ነው፤ ቋንቋቸውንም የማታውቀው፥ የሚናገሩትንም የማታስተውለው ሕዝብ ነው።
ሕዝቡ ሁሉ በአንድነት ቢሰበሰቡ፥ ሁሉም በልዩ ልዩ ቋንቋ ቢናገሩ፥ አላዋቂዎች፥ ወይም የማያምኑ ቢመጡ አብደዋል ይሉአቸው የለምን?