La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ገላትያ 3:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እርሱ መን​ፈስ ቅዱ​ስን የሚ​ሰ​ጣ​ችሁ፥ ኀይ​ል​ንም የሚ​ያ​ደ​ር​ግ​ላ​ችሁ የኦ​ሪ​ትን ሥራ በመ​ሥ​ራት ነውን? ወይስ ሃይ​ማ​ኖ​ትን በመ​ስ​ማት ነው?

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔር መንፈሱን የሚሰጣችሁ፣ በእናንተም ዘንድ ታምራትን የሚሠራው ሕግን ስለ ጠበቃችሁ ነው ወይስ የሰማችሁትን ስላመናችሁ?

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እንግዲህ መንፈስን የሚሰጣችሁ በእናንተም ድንቅን የሚሠራ፥ በሕግ ሥራ ነውን? ወይስ በእምነት በመስማታችሁ ነው?

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔር መንፈሱን የሚሰጣችሁና በእናንተ ዘንድ ተአምራትን የሚያደርገው ሕግን በመፈጸማችሁ ነውን? ወይስ የምሥራቹን ቃል ሰምታችሁ በማመናችሁ ነው?

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እንግዲህ መንፈስን የሚሰጣችሁ በእናንተም ዘንድ ተአምራት የሚያደርግ፥ በሕግ ሥራ ነውን ወይስ ከእምነት ጋር በሆነ መስማት ነው?

Ver Capítulo



ገላትያ 3:5
14 Referencias Cruzadas  

በጌ​ታም ፊት ደፍ​ረው እያ​ስ​ተ​ማሩ፥ እር​ሱም የጸ​ጋ​ውን ቃል ምስ​ክር እያ​ሳ​የ​ላ​ቸው፥ በእ​ጃ​ቸ​ውም ድንቅ ሥራና ተአ​ም​ራ​ትን እያ​ደ​ረ​ገ​ላ​ቸው ብዙ ወራት ኖሩ።


ማመን ከመ​ስ​ማት ነው፤ መስ​ማ​ትም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ነው።


በኀ​ይ​ልና በተ​አ​ም​ራት፥ በመ​ን​ፈስ ቅዱስ ኀይ​ልና ድንቅ ሥራን በመ​ሥ​ራ​ትም፥ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አው​ራ​ጃ​ዎች ጀምሬ እስከ እል​ዋ​ሪ​ቆን ድረስ እንደ አስ​ተ​ማ​ርሁ፥ የክ​ር​ስ​ቶ​ስ​ንም ወን​ጌል ፈጽሞ እንደ ሰበ​ክሁ እና​ገር ዘንድ እደ​ፍ​ራ​ለሁ።


ለአ​ን​ዱም ተአ​ም​ራ​ትን ማድ​ረግ፥ ለአ​ን​ዱም ትን​ቢ​ትን መና​ገር፥ ለአ​ን​ዱም መና​ፍ​ስ​ትን መለ​የት፥ ለአ​ን​ዱም በልዩ ዓይ​ነት ልሳን መና​ገር፥ ለአ​ን​ዱም በል​ሳ​ኖች የተ​ነ​ገ​ረ​ውን መተ​ር​ጐም ይሰ​ጠ​ዋል።


የጦር ዕቃ​ችን ሥጋዊ አይ​ደ​ለ​ምና፥ ጽኑ ምሽ​ግን በሚ​ያ​ፈ​ርስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይል ነው እንጂ።


የሐ​ዋ​ር​ያት ምል​ክ​ትስ በፍ​ጹም ትዕ​ግ​ሥ​ትና በተ​አ​ም​ራት፥ ድንቅ ሥራ በመ​ሥ​ራ​ትና በኀ​ይ​ላት ተደ​ር​ጎ​ላ​ች​ኋል።


ክር​ስ​ቶስ በእኔ አድሮ እን​ደ​ሚ​ና​ገር ማስ​ረጃ ትሻ​ላ​ች​ሁና፤ እር​ሱም ሁሉ የሚ​ቻ​ለው ነው እንጂ፥ በእ​ና​ንተ ዘንድ የሚ​ሳ​ነው የለም።


ለመ​ን​ፈስ ቅዱስ መል​እ​ክ​ትማ ምንኛ እጅግ ክብር ሊደ​ረግ ይገባ ይሆን?


እርሱ ዘርን ለዘሪ ይሰ​ጣል፤ እህ​ል​ንም ለም​ግብ ይሰ​ጣ​ች​ኋል፤ ዘራ​ች​ሁ​ንም ያበ​ዛ​ላ​ች​ኋል፤ የጽ​ድ​ቃ​ች​ሁ​ንም መከር ያበ​ጃል።


በእ​ና​ንተ ዘንድ ይህን ብቻ ላውቅ እወ​ድ​ዳ​ለሁ፤ መን​ፈስ ቅዱ​ስን የተ​ቀ​በ​ላ​ችሁ የኦ​ሪ​ትን ሥራ በመ​ሥ​ራት ነውን? ወይስ ሃይ​ማ​ኖ​ትን በመ​ስ​ማት?


እኔም ይህቺ ሥራ በጸ​ሎ​ታ​ች​ሁና በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ መን​ፈስ ወደ ሕይ​ወት እን​ደ​ም​ታ​ደ​ር​ሰኝ አው​ቃ​ለሁ።