ሕዝቡም ሁሉ እርሱን ተከትለው ወጡ፤ ከበሮንና መሰንቆንም መቱ፥ በታላቅም ደስታ ደስ አላቸው፤ ከጩኸታቸውም የተነሣ ምድር ተናወጠች።
ዕዝራ 3:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደስ ብሎአቸው የሚጮኹትን ድምፅ ከሕዝቡ ልቅሶ ድምፅ መለየት የሚችል አልነበረም፥ ሕዝቡ በታላቅ ድምፅ ይጮኽ ነበርና ድምፁም ከሩቅ ይሰማ ነበርና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሕዝቡ ጩኸት ድብልቅልቅ ያለ ስለ ነበር፣ የደስታውን እልልታ ከልቅሶው ጩኸት መለየት የሚችል ማንም አልነበረም፤ ድምፁም ከሩቅ ይሰማ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕዝቡ ግን ደስ ብሎአቸው የሚጮኹትን ድምፅ ከሕዝቡ ልቅሶ ድምፅ መለየት አልቻለም፤ ሕዝቡም በታላቅ ድምፅ እልል ይሉ ነበር፥ ድምፁም ከሩቅ ይሰማ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሚያሰሙት ከፍተኛ ድምፅ በስፋት እስከ ሩቅ ያስተጋባ ስለ ነበር ማንም ሰው የደስታውን እልልታና የለቅሶውን ጩኸት ድምፅ ለመለየት አልተቻለውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደስ ብሎአቸው የሚጮኹትን ድምፅ ከሕዝቡ ልቅሶ ድምፅ መለየት የሚችል አልነበረም፤ ሕዝቡም በታላቅ ድምፅ ይጮኽ ነበር፤ ድምፁም ከሩቅ ይሰማ ነበር። |
ሕዝቡም ሁሉ እርሱን ተከትለው ወጡ፤ ከበሮንና መሰንቆንም መቱ፥ በታላቅም ደስታ ደስ አላቸው፤ ከጩኸታቸውም የተነሣ ምድር ተናወጠች።
ካህኑም ሳዶቅና ነቢዩ ናታን ቀብተው በግዮን አነገሡት፤ ከዚያም ደስ ብሎአቸው ወጡ፤ ከተማዪቱም አስተጋባች፤ የሰማችሁትም ድምፅ ይህ ነው።
የፊተኛውን ቤት ያዩ ሽማግሌዎች የሆኑ ብዙ ካህናትና ሌዋውያን፥ የአባቶችም ቤቶች አለቆች ግን ይህ መቅደስ በፊታቸው በተመሠረተ ጊዜ በታላቅ ድምፅ ያለቅሱ ነበር፤ ብዙ ሰዎችም እየዘመሩ በደስታ ይጮኹ ነበር፤
የይሁዳና የብንያምም ጠላቶች፥ የምርኮኞቹ ልጆች ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር መቅደስ እንደሚሠሩ ሰሙ።
እግዚአብሔርም በታላቅ ደስታ ደስ አሰኝቶአቸዋልና በዚያ ቀን ትልቅ መሥዋዕት አቀረቡ፤ ደስም አላቸው፤ ሴቶቹና ልጆቹም ደግሞ ደስ አላቸው፤ ደስታቸውም በኢየሩሳሌም ከሩቅ ተሰማ።
በአንተ የሚታመኑት ሁሉ ግን ደስ ይላቸዋል፤ ለዘለዓለሙ ደስ ይላቸዋል፥ በእነርሱም ታድራለህ። ስምህንም የሚወድዱ ሁሉ በአንተ ይመካሉ።
የሐሤት ድምፅና የደስታ ድምፅ፥ የወንድ ሙሽራ ድምፅና የሴት ሙሽራ ድምፅ፦ እግዚአብሔር ቸር ነውና፥ ምሕረቱም ለዘለዓለም ነውና የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን አመስግኑ የሚሉ ሰዎች ድምፅ፥ ወደ እግዚአብሔርም ቤት የምስጋናን መሥዋዕት የሚያመጡ ሰዎች ድምፅ እንደ ገና ይሰማል። የዚያችን ምድር ምርኮኞች ቀድሞ እንደ ነበረ አድርጌ እመልሳለሁና፥” ይላል እግዚአብሔር።
“በዚያም ወራት በዚያም ጊዜ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ የእስራኤል ልጆችና የይሁዳ ልጆች በአንድነት ሆነው ይመጣሉ፤ እያለቀሱም መንገዳቸውን ይሄዳሉ፥ አምላካቸውንም እግዚአብሔርን ይፈልጋሉ።
ታላቅ ተራራ ሆይ፥ አንተ ምንድር ነህ? በዘሩባቤል ፊት ደልዳላ ሜዳ ትሆናለህ፣ ሰዎችም፦ ሞገስ፥ ሞገስ ይሁንለት ብለው እየጮኹ እርሱ መደምደሚያውን ድንጋይ ያወጣል ብሎ ተናገረኝ።
የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት ወደ ሰፈር በገባች ጊዜ እስራኤል ሁሉ ታላቅ እልልታ አደረጉ፤ ምድሪቱም አስተጋባች።