Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዕዝራ 3:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 የሚያሰሙት ከፍተኛ ድምፅ በስፋት እስከ ሩቅ ያስተጋባ ስለ ነበር ማንም ሰው የደስታውን እልልታና የለቅሶውን ጩኸት ድምፅ ለመለየት አልተቻለውም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 የሕዝቡ ጩኸት ድብልቅልቅ ያለ ስለ ነበር፣ የደስታውን እልልታ ከልቅሶው ጩኸት መለየት የሚችል ማንም አልነበረም፤ ድምፁም ከሩቅ ይሰማ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ሕዝቡ ግን ደስ ብሎአቸው የሚጮኹትን ድምፅ ከሕዝቡ ልቅሶ ድምፅ መለየት አልቻለም፤ ሕዝቡም በታላቅ ድምፅ እልል ይሉ ነበር፥ ድምፁም ከሩቅ ይሰማ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ደስ ብሎ​አ​ቸው የሚ​ጮ​ኹ​ትን ድምፅ ከሕ​ዝቡ ልቅሶ ድምፅ መለ​የት የሚ​ችል አል​ነ​በ​ረም፥ ሕዝቡ በታ​ላቅ ድምፅ ይጮኽ ነበ​ርና ድም​ፁም ከሩቅ ይሰማ ነበ​ርና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ደስ ብሎአቸው የሚጮኹትን ድምፅ ከሕዝቡ ልቅሶ ድምፅ መለየት የሚችል አልነበረም፤ ሕዝቡም በታላቅ ድምፅ ይጮኽ ነበር፤ ድምፁም ከሩቅ ይሰማ ነበር።

Ver Capítulo Copiar




ዕዝራ 3:13
14 Referencias Cruzadas  

የቃል ኪዳኑም ታቦት በዚያ ቦታ በደረሰ ጊዜ እስራኤላውያን ምድር እስክትናወጥ ድረስ ታላቅ የእልልታና የሆታ ድምፅ አሰሙ።


እንደ ተራራ በፊትህ የተደቀነው መሰናክል ሁሉ ይወገዳል፤ ቤተ መቅደሱንም መልሰህ ትሠራለህ፤ የመደምደሚያውንም ድንጋይ በስፍራው መልሰህ በምታኖርበት ጊዜ ሕዝቡ ‘እንዴት ውብ ነው! ውብ ነው!’ እያሉ የደስታ ድምፅ ያሰማሉ።”


በዚህ ቦታ የተድላና የደስታ፥ የሠርግ ዘፈን ድምፅ እንደገና ይሰማል፤ ከምርኮ ለተመለሱትም ቀድሞ የነበራቸውን ንብረታቸውን ስለምመልስላቸው የምስጋና መሥዋዕት ለማቅረብ ወደ ቤተ መቅደሴ በሚመጡበት ጊዜ፥ ‘የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ እርሱ ቸር ነውና፥ ፍቅሩም ዘለዓለማዊ ነውና’ እያሉ በከፍተኛ ድምፅ ይዘምራሉ። ይህን የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”


በአንተ ከለላ ሥር ያሉ ሁሉ ይደሰቱ፤ ለዘለዓለምም እልል ይበሉ የአንተን ስም የሚወዱትን ሁሉ በደስታም እንዲፈነድቁ ከልላቸው።


በዚያም ዕለት ብዙ መሥዋዕት ቀረበ፤ ሕዝቡም እግዚአብሔር ደስ ስላሰኛቸው ታላቅ ሐሴት አደረጉ፤ ሴቶችም፥ ልጆችም አብረው ተደስተዋል፤ በኢየሩሳሌም የነበረው የእልልታቸው ድምፅ እስከ ሩቅ ድረስ ይሰማ ነበር።


ካህኑ ሳዶቅና ነቢዩ ናታን በግዮን ምንጭ አጠገብ ቀብተው አንግሠውታል፤ ከዚህም በኋላ ሕዝቡ ሁሉ በደስታ ተሞልተው በእልልታና በሆታ ድምፃቸው እያስተጋባ ወደ ከተማ ተመልሰዋል፤ አሁን የምትሰሙትም ድምፅ ይኸው ነው፤


ወደ ቤተ መንግሥትም በሚመለሱበት ጊዜ አጅበው ተከተሉት፤ ከድምፃቸው ከፍተኛነት የተነሣ ምድር እስክትናወጥ ድረስ እምቢልታ በመንፋት እየጮኹ ደስታቸውን ገለጡ።


ያ ስፍራ “ቦኪም” ተብሎ የተጠራውም በዚህ ምክንያት ነው፤ በዚያም ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አቀረቡ።


ከሽማግሌዎቹ ካህናትና ሌዋውያን ብዙዎቹ እንዲሁም የጐሣ መሪዎች የቀድሞውን ቤተ መቅደስ አሠራር በዐይናቸው አይተው ስለ ነበር የዚህኛውን ቤተ መቅደስ መሠረት ሲጣል ባዩ ጊዜ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አለቀሱ፤ በዚያ የነበሩት የሌሎቹ እልልታ ግን አስተጋባ።


የይሁዳና የብንያም ሕዝብ ጠላቶች የሆኑ ነዋሪዎች ከምርኮ የተመለሱት ሰዎች ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ በመሥራት ላይ መሆናቸውን ሰሙ።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ዘመኑና ጊዜው ሲደርስ የእስራኤልና የይሁዳ ሕዝብ በአንድነት ሆነው እኔን አምላካቸውን ፍለጋ እያለቀሱ ይመጣሉ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios