Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ነገሥት 1:45 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

45 ካህ​ኑም ሳዶ​ቅና ነቢዩ ናታን ቀብ​ተው በግ​ዮን አነ​ገ​ሡት፤ ከዚ​ያም ደስ ብሎ​አ​ቸው ወጡ፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱም አስ​ተ​ጋ​ባች፤ የሰ​ማ​ች​ሁ​ትም ድምፅ ይህ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

45 ካህኑ ሳዶቅና ነቢዩ ናታን በግዮን ቀብተው አንግሠውታል። ከዚያም ደስ ብሏቸው ወጥተዋል፤ ከተማዪቱም ይህንኑ አስተጋብታለች፤ እንግዲህ የሰማችሁት ድምፅ ይኸው ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

45 ካህኑም ሳዶቅና ነቢዩ ናታን በግዮን ንጉሥ አድርገው ቀቡት፥ ከዚያም ደስ ብሎአቸው ወጡ፥ ከተማይቱም አስተጋባች፥ የሰማችሁትም ድምፅ ይህ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

45 ካህኑ ሳዶቅና ነቢዩ ናታን በግዮን ምንጭ አጠገብ ቀብተው አንግሠውታል፤ ከዚህም በኋላ ሕዝቡ ሁሉ በደስታ ተሞልተው በእልልታና በሆታ ድምፃቸው እያስተጋባ ወደ ከተማ ተመልሰዋል፤ አሁን የምትሰሙትም ድምፅ ይኸው ነው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

45 ካህኑም ሳዶቅና ነቢዩ ናታን በግዮን ንጉሥ አድርገው ቀቡት፤ ከዚያም ደስ ብሎአቸው ወጡ፤ ከተማይቱም አስተጋባች፤ የሰማችሁትም ድምጽ ይህ ነው።

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 1:45
7 Referencias Cruzadas  

ሕዝ​ቡም ሁሉ እር​ሱን ተከ​ት​ለው ወጡ፤ ከበ​ሮ​ንና መሰ​ን​ቆ​ንም መቱ፥ በታ​ላ​ቅም ደስታ ደስ አላ​ቸው፤ ከጩ​ኸ​ታ​ቸ​ውም የተ​ነሣ ምድር ተና​ወ​ጠች።


ንጉ​ሡም ከእ​ርሱ ጋር ካህ​ኑን ሳዶ​ቅ​ንና ነቢ​ዩን ናታ​ንን፥ የዮ​ዳ​ሄ​ንም ልጅ በና​ያ​ስን፥ ከሊ​ታ​ው​ያ​ን​ንና ፈሊ​ታ​ው​ያ​ን​ንም ላከ፤ በን​ጉ​ሡም በቅሎ ላይ አስ​ቀ​መ​ጡት።


እር​ስ​ዋም በደጅ ስት​ገባ አኪያ የእ​ግ​ር​ዋን ኮቴ ሰማ፤ እን​ዲ​ህም አላት፥ “የኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ሚስት ሆይ፥ ግቢ! ስለ​ም​ንስ ራስ​ሽን ለወ​ጥሽ? እኔም የሚ​ያ​ስ​ጨ​ንቅ ወሬ ይዤ ወደ አንቺ ተል​ኬ​አ​ለሁ።


ደስ ብሎ​አ​ቸው የሚ​ጮ​ኹ​ትን ድምፅ ከሕ​ዝቡ ልቅሶ ድምፅ መለ​የት የሚ​ችል አል​ነ​በ​ረም፥ ሕዝቡ በታ​ላቅ ድምፅ ይጮኽ ነበ​ርና ድም​ፁም ከሩቅ ይሰማ ነበ​ርና።


እር​ሱም፥ “ምን አየሽ?” አላት። እር​ስ​ዋም፥ “ቀጥ ያለ ሽማ​ግሌ ሰው ከም​ድር ወጣ፤ መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያም ተጐ​ና​ጽ​ፎ​አል” አለች። ሳኦ​ልም ሳሙ​ኤል እንደ ሆነ ዐወቀ፤ በፊ​ቱም ወደ ምድር ጐን​በስ ብሎ ሰገ​ደ​ለት።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቃል ኪዳን ታቦት ወደ ሰፈር በገ​ባች ጊዜ እስ​ራ​ኤል ሁሉ ታላቅ እል​ልታ አደ​ረጉ፤ ምድ​ሪ​ቱም አስ​ተ​ጋ​ባች።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos