Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዕዝራ 3:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 የፊ​ተ​ኛ​ውን ቤት ያዩ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች የሆኑ ብዙ ካህ​ና​ትና ሌዋ​ው​ያን፥ የአ​ባ​ቶ​ችም ቤቶች አለ​ቆች ግን ይህ መቅ​ደስ በፊ​ታ​ቸው በተ​መ​ሠ​ረተ ጊዜ በታ​ላቅ ድምፅ ያለ​ቅሱ ነበር፤ ብዙ ሰዎ​ችም እየ​ዘ​መሩ በደ​ስታ ይጮኹ ነበር፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 የቀድሞውን ቤተ መቅደስ ያዩ በዕድሜ የሸመገሉ ብዙ ካህናት፣ ሌዋውያንና የቤተ ሰብ አለቆች የዚህ ቤተ መቅደስ መሠረት ሲጣል ባዩ ጊዜ፣ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አለቀሱ፤ ሌሎቹ ግን የደስታ ጩኸት አሰሙ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 የመጀመሪያውን ቤት ያዩ ብዙ ካህናት፥ ሌዋውያን፥ የአባቶች አለቆችና ሽማግሌዎች ግን ይህ ቤት በፊታቸው በተመሠረተ ጊዜ በታላቅ ድምፅ ያለቅሱ ነበር፥ ብዙ ሰዎችም በደስታ እልል ይሉ ነበር፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ከሽማግሌዎቹ ካህናትና ሌዋውያን ብዙዎቹ እንዲሁም የጐሣ መሪዎች የቀድሞውን ቤተ መቅደስ አሠራር በዐይናቸው አይተው ስለ ነበር የዚህኛውን ቤተ መቅደስ መሠረት ሲጣል ባዩ ጊዜ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አለቀሱ፤ በዚያ የነበሩት የሌሎቹ እልልታ ግን አስተጋባ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 የፊተኛውን ቤት ያዩ ሽማግሌዎች የሆኑ ብዙ ካህናትና ሌዋውያን፥ የአባቶችም ቤቶች አለቆች ግን ይህ መቅደስ በፊታቸው በተመሠረተ ጊዜ በታላቅ ድምፅ ያለቅሱ ነበር፤ ብዙ ሰዎችም በደስታ ይጮኹ ነበር፤

Ver Capítulo Copiar




ዕዝራ 3:12
12 Referencias Cruzadas  

በቀድሞ ክብሩ ሳለ ይህን ቤት ያየ በእናንተ መካከል የቀረ ማን ነው? ዛሬስ እንዴት ሆኖ አያችሁት? በዓይናችሁ እንደ ምናምን አይደለምን?


የጥቂቱን ነገር ቀን የናቀ ማን ነው? እነዚህ ሰባቱ ደስ ብሎአቸው በዘሩባቤል እጅ ቱንቢውን ያያሉ፣ እነዚህም በምድር ሁሉ የሚዘዋወሩ የእግዚአብሔር ዓይኖች ናቸው።


ታናሹ ሺህ፥ የሁ​ሉም ታናሽ ታላቅ ሕዝብ ይሆ​ናል፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዘ​መ​ና​ቸው ሁሉ እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ።


ያዕ​ቆብ ሆይ፥ አት​ፍራ፤ በቍ​ጥር ጥቂት የነ​በ​ርህ እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ እኔ እረ​ዳ​ሃ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ የሚ​ቤ​ዥ​ህም የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ ነው።


ጅማ​ሬ​ህም ታናሽ ቢሆ​ንም እንኳ ፍጻ​ሜህ ቍጥር አይ​ኖ​ረ​ውም።


ደስ ብሎ​አ​ቸው የሚ​ጮ​ኹ​ትን ድምፅ ከሕ​ዝቡ ልቅሶ ድምፅ መለ​የት የሚ​ችል አል​ነ​በ​ረም፥ ሕዝቡ በታ​ላቅ ድምፅ ይጮኽ ነበ​ርና ድም​ፁም ከሩቅ ይሰማ ነበ​ርና።


“በዚ​ያም ወራት በዚ​ያም ጊዜ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችና የይ​ሁዳ ልጆች በአ​ን​ድ​ነት ሆነው ይመ​ጣሉ፤ እያ​ለ​ቀ​ሱም መን​ገ​ዳ​ቸ​ውን ይሄ​ዳሉ፥ አም​ላ​ካ​ቸ​ው​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ይፈ​ል​ጋሉ።


ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኚ፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios