ካህናቱም ሰበንያ፥ ኢዮሣፍጥ፥ ናትናኤል፥ ዓማሣይ፥ ዘካርያስ፥ በናያስ፥ አልዓዛርም በእግዚአብሔር ታቦት ፊት መለከት ይነፉ ነበር። አብዲዶምና ኢያኤያም የእግዚአብሔር ታቦት በረኞች ነበሩ።
ዕዝራ 3:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አናጢዎቹም የእግዚአብሔርን መቅደስ ይሠሩ ዘንድ መሠረት በጣሉ ጊዜ ካህናቱ ልብሳቸውን ለብሰው መለከቱን ይዘው፥ የአሳፍም ልጆች ሌዋውያን ጸናጽል ይዘው እንደ እስራኤል ንጉሥ እንደ ዳዊት ሥርዐት እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ዘንድ ቆሙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ግንበኞቹ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ መሠረት በጣሉ ጊዜ፣ ካህናቱ ልብሰ ተክህኗቸውን ለብሰውና መለከታቸውን ይዘው፣ ሌዋውያኑ የአሳፍ ልጆች ደግሞ ጸናጽል ይዘው፣ በእስራኤል ንጉሥ በዳዊት መመሪያ መሠረት እግዚአብሔርን ለመወደስ ስፍራቸውን ያዙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ግንበኞቹም የጌታን መቅደስ መሠረቱ፤ ካህናቱ ሙሉ ልብስ ለብሰው፥ መለከት ይዘው፥ የአሳፍ ልጆች ሌዋውያን ጸናጽል ይዘው በእስራኤል ንጉሥ በዳዊት መመሪያ መሠረት ጌታን እንዲያመሰግኑ መረጧቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሠራተኞቹ የቤተ መቅደሱን መሠረት ማኖር በጀመሩበት ጊዜ ካህናቱ ልብሰ ተክህኖአቸውን ለብሰው በእጃቸው እምቢልታ በመያዝ የአሳፍ ቤተሰብ ተወላጆች የሆኑ ሌዋውያንም ጸናጽል ይዘው በረድፍ ቆመው ነበር፤ እነርሱም ከንጉሥ ዳዊት ዘመን ጀምሮ ተያይዞ በመጣው መመሪያ መሠረት በመዝሙር እግዚአብሔርን አመሰገኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አናጢዎቹም የእግዚአብሔርን መቅደስ በመሠረቱ ጊዜ ካህናቱ ልብሳቸውን ለብሰው፥ መለከቱን ይዘው፥ የአሳፍም ልጆች ሌዋውያን ጸናጽል ይዘው እንደ እስራኤል ንጉሥ እንደ ዳዊት ሥርዓት እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ዘንድ ቆሙ። |
ካህናቱም ሰበንያ፥ ኢዮሣፍጥ፥ ናትናኤል፥ ዓማሣይ፥ ዘካርያስ፥ በናያስ፥ አልዓዛርም በእግዚአብሔር ታቦት ፊት መለከት ይነፉ ነበር። አብዲዶምና ኢያኤያም የእግዚአብሔር ታቦት በረኞች ነበሩ።
ዳዊትም፥ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙ ሌዋውያንም ሁሉ፥ መዘምራኑም፥ የመዘምራኑም አለቃ ኮኖንያስ የጥሩ በፍታ ቀሚስ ለብሰው ነበር፤ ዳዊትም የከበረ ልብስ ለብሶ ነበረ።
ከእነርሱም ጋር ካህናቱ ከፍ አድርገው ለማሰማት መለከትና ጸናጽል ለእግዚአብሔርም መዝሙራት የዜማ ዕቃ ይዘው ነበር፤ የኤዶታም ልጆች ግን በረኞች ነበሩ።
ከዚያም በኋላ ለራሳቸውና ከእነርሱ ጋር ላሉ ለካህናቱ አዘጋጁ፤ የአሮንም ልጆች ካህናቱ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና ስቡን ለማቅረብ እስከ ሌሊት ድረስ ይሠሩ ነበርና ስለዚህ ሌዋውያን ለራሳቸውና ለወንድሞቻቸው ለአሮን ልጆች ለካህናቱ አዘጋጁ።
የአሳፍም ልጆች መዘምራን እንደ ዳዊት፥ እንደ አሳፍም፥ እንደ ኤማንም የንጉሡም ባለ ራእይ እንደ ነበረው እንደ ኤዶትም ትእዛዝ በየስፍራቸው ነበሩ፤ በረኞቹም በሮቹን ሁሉ ይጠብቁ ነበር፤ ወንድሞቻቸውም ሌዋውያን ያዘጋጁላቸው ነበርና ከአገልግሎታቸው ይርቁ ዘንድ አያስፈልጋቸውም ነበር።
መዘምራንም የነበሩት ሌዋውያን ሁሉ፥ ከአሳፍና ከኤማን፥ ከኤዶትምም ልጆች ጋር ወንድሞቻቸውም፥ ጥሩ በፍታ ለብሰው ጸናጽልና ከበሮ፥ መሰንቆም እየመቱ በመሠዊያው አጠገብ በምሥራቅ በኩል ቆመው ነበር፤ ከእነርሱም ጋር መቶ ሃያ ካህናት መለከት ይነፉ ነበር።
በዚያ ጊዜም ይህ ሲሳብሳር መጣ፤ በኢየሩሳሌምም ያለውን የእግዚአብሔርን ቤት መሠረተ፤ ከዚያም ጊዜ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እየተሠራ አልተጨረሰም።
የጥቂቱን ነገር ቀን የናቀ ማን ነው? እነዚህ ሰባቱ ደስ ብሎአቸው በዘሩባቤል እጅ ቱንቢውን ያያሉ፣ እነዚህም በምድር ሁሉ የሚዘዋወሩ የእግዚአብሔር ዓይኖች ናቸው።
መልሶም፦ ለዘሩባቤል የተባለው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፦ በመንፈሴ እንጂ በኃይልና በብርታት አይደለም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
ታላቅ ተራራ ሆይ፥ አንተ ምንድር ነህ? በዘሩባቤል ፊት ደልዳላ ሜዳ ትሆናለህ፣ ሰዎችም፦ ሞገስ፥ ሞገስ ይሁንለት ብለው እየጮኹ እርሱ መደምደሚያውን ድንጋይ ያወጣል ብሎ ተናገረኝ።
ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር ቤት ካህናት ለነቢያትም፦ ባለፉት ዓመታት እንዳደረግሁት በአምስተኛው ወር መለየትና ማልቀስ ይገባኛልን? ብለው ይናገሩ ዘንድ ልኮአቸው ነበር።
ንጉሡም ዶይቅን፥ “አንተ ዞረህ ካህናቱን ግደላቸው” አለው። ሶርያዊው ዶይቅም ዞሮ ካህናቱን ገደላቸው፤ በዚያም ቀን የበፍታ ኤፉድ የለበሱትን ሦስት መቶ ሰማንያ አምስት ሰዎችን ገደለ።