La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዕዝራ 1:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በዙ​ሪ​ያ​ቸ​ውም ያሉ ሁሉ በፈ​ቃ​ዳ​ቸው ካቀ​ረ​ቡት ሁሉ ሌላ በብር ዕቃና በወ​ርቅ፥ በገ​ን​ዘ​ቦ​ችና በእ​ን​ስ​ሶች፥ በሌ​ላም ስጦታ ይረ​ዷ​ቸው ነበር።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ጎረቤቶቻቸውም ሁሉ በበጎ ፈቃድ ከሰጡት መባ በተጨማሪ ከብርና ከወርቅ የተሠሩ ዕቃዎችን፣ ቍሳቍስን፣ እንስሳትንና ሌሎች ጠቃሚ የሆኑ ስጦታዎችንም በመለገስ ረዷቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በዙሪያቸውም ያሉ ሁሉ በፈቃዳቸው ካቀረቡት መባ ሁሉ በተጨማሪ በእጃቸው፥ በብር ዕቃና በወርቅ፥ በዕቃዎችና በእንስሶችና በውድ ነገሮች አበረታቱአቸው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ጐረቤቶቻቸውም ከብርና ከወርቅ የተሠሩ ዕቃዎችን፥ ቈሳቊሶችንና ከብቶችን፥ ሌሎችንም ጠቃሚ የሆኑ ስጦታዎችና በቤተ መቅደስ መባ ሆኖ የሚቀርብ ሌላም ነገር በመለገሥ ረዱአቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በዙሪያቸውም ያሉ ሁሉ በፈቃዳቸው ካቀረቡት ሁሉ ሌላ በብር ዕቃና፥ በወርቅ፥ በቍሳቍሶችና በእንስሶች በሌላም ስጦታ አገዙአቸው።

Ver Capítulo



ዕዝራ 1:6
12 Referencias Cruzadas  

ሕዝ​ቡም ፈቅ​ደው ሰጥ​ተ​ዋ​ልና፥ በፍ​ጹም ልባ​ቸ​ውም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፈ​ቃ​ዳ​ቸው አቅ​ር​በ​ዋ​ልና ደስ አላ​ቸው፤ ንጉ​ሡም ዳዊት ደግሞ ታላቅ ደስታ ደስ አለው።


በስ​ደት በሚ​ኖ​ር​ባ​ቸው ከተ​ሞች ሁሉ ለቀ​ረው ሰው ሁሉ የሀ​ገሩ ሰዎች በብ​ርና በወ​ርቅ፥ በዕ​ቃም፥ በእ​ን​ስ​ሳም ይር​ዱት፤ ይህም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላለው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በፈ​ቃ​ዳ​ቸው ከሚ​ያ​ቀ​ር​ቡት ሌላ ይሁን።”


በአ​ራ​ተ​ኛ​ውም ቀን ብሩና ወርቁ፥ ዕቃ​ዎ​ቹም በአ​ም​ላ​ካ​ችን ቤት በካ​ህኑ በኦ​ርያ ልጅ በሜ​ሪ​ሞት እጅ ተመ​ዘኑ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር የፊ​ን​ሐስ ልጅ አል​ዓ​ዛር ነበረ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ሌዋ​ው​ያን የኢ​ያሱ ልጅ ኢዮ​ዛ​ብ​ድና የቤ​ንዊ ልጅ ናሕ​ድያ ነበሩ።


እነ​ር​ሱም ሁሉ ሥራው እን​ዳ​ይ​ፈ​ጸም፥ “እጃ​ቸው ይደ​ክ​ማል” ብለው አስ​ፈ​ራ​ሩን፤ ስለ​ዚ​ህም እጆ​ችን አበ​ረ​ታሁ።


ሥራው ምስ​ጋ​ናና የጌ​ት​ነት ክብር ነው። ጽድ​ቁም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ራል።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሙሴ እን​ዳ​ዘዘ አደ​ረጉ። ከግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንም የብ​ር​ንና የወ​ር​ቅን ዕቃ፥ ልብ​ስ​ንም ተዋሱ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለሕ​ዝቡ በግ​ብ​ፃ​ው​ያን ፊት ሞገ​ስን ሰጠ፤ እነ​ር​ሱም አዋ​ሱ​አ​ቸው። እነ​ር​ሱም ግብ​ፃ​ው​ያ​ንን በዘ​በ​ዙ​አ​ቸው።


ደካ​ሞች እጆ​ችና አን​ካ​ሶች ጕል​በ​ቶች፥ ጽኑ።


ሁሉ ልቡ እንደ ወደደ ያድ​ርግ፤ በደ​ስታ ይስጡ እንጂ በግድ አይ​ሆ​ንም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በደ​ስታ የሚ​ሰ​ጠ​ውን ይወ​ዳ​ልና።