ዘፀአት 9:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም በግብፅ ሀገር ሁሉ ትቢያ ይሆናል፤ በግብፅም ሀገር ሁሉ በሰውና በእንስሳ ላይ ሻህኝ የሚያመጣ ቍስል ይሆናል” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በግብጽ ምድር ሁሉ ትቢያ ይሆናል፤ በምድሪቱ ሁሉ በሚገኙት ሰዎችና እንስሳት ላይ መግል የያዘ ዕባጭ ይወጣል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም በግብጽ ምድር ሁሉ ትቢያ ይሆናል፥ በግብጽም ምድር ሁሉ በሰውና በእንስሳ ላይ ፈሳሽ የሚያወጣ ብጉንጅ ይሆናል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱም እንደ ደቃቅ ትቢያ ሆኖ በግብጽ ምድር ሁሉ ላይ በሚሠራጭበት ጊዜ በሕዝብና በእንስሶቹ ላይ አሠቃቂ የሆነ ብርቱ ቊስል ያመጣል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም በግብፅ አገር ሁሉ ትቢያ ይሆናል፥ በግብፅም አገር ሁሉ በሰውና በእንስሳ ላይ ሻህኝ የሚያመጣ ቁስል ይሆናል አላቸው፤” |
እግዚአብሔርም ሙሴንና አሮንን፥ “እጃችሁን ሞልታችሁ ከምድጃ አመድ ውሰዱ፤ ሙሴም በፈርዖንና በሹሞቹ ፊት ወደ ሰማይ ይበትነው።
እግዚአብሔር ልትድን በማትችልበት በክፉ ቍስል ጕልበትህንና ጭንህን ከእግርህ ጫማ እስከ አናትህ ድረስ ይመታሃል።