Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘዳግም 28:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

35 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልት​ድን በማ​ት​ች​ል​በት በክፉ ቍስል ጕል​በ​ት​ህ​ንና ጭን​ህን ከእ​ግ​ርህ ጫማ እስከ አና​ትህ ድረስ ይመ​ታ​ሃል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

35 እግዚአብሔር ከእግርህ ጥፍር እስከ ራስህ ጠጕር በሚዛመት፣ ሊድን በማይችልና በሚያሠቃይ ቍስል ጕልበትህንና እግርህን ይመታሃል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

35 ጌታ ከእግርህ ጥፍር እስከ ራስህ ጠጉር በሚዛመት፥ ሊድን በማይችልና በሚያሠቃይ ቁስል ጉልበትህንና እግርህን ይመታሃል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

35 እግዚአብሔር ቅልጥምህንና ጭንህን በማይፈወስ ቊስል እንዲሸፈን ያደርጋል፤ ብርቱ ቊስልና እባጭ ከራስ ጠጒርህ እስከ እግር ጥፍርህ ይሸፍንሃል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

35 እግዚአብሔር ፈውስ በሌለው በክፉ ቁስል ጉልበትህንና ጭንህን ከእግርህ ጫማ እስከ አናትህ ድረስ ይመታሃል።

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 28:35
8 Referencias Cruzadas  

በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ዘንድ እንደ አቤ​ሴ​ሎም በው​በቱ ያማረ ሰው አል​ነ​በ​ረም፤ ከእ​ግሩ እስከ ራሱ ድረስ ነውር አል​ነ​በ​ረ​በ​ትም።


ከእ​ግር ጫማ አን​ሥቶ እስከ ራስ ድረስ ጤና የለ​ውም፤ ቍስ​ልና እበጥ የሚ​መ​ግ​ልም ነው፤ አል​ፈ​ረ​ጠም፤ አል​ተ​ጠ​ገ​ነ​ምም፤ በዘ​ይ​ትም አል​ለ​ዘ​በም።


ስለ​ዚህ ጌታ የጽ​ዮን ታላ​ላቅ ሴቶች ልጆ​ችን ያዋ​ር​ዳ​ቸ​ዋል። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዚያ ቀን ልብ​ሳ​ቸ​ውን ይገ​ል​ጣል።


እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ ስለ ሥራሽ ክፋት በሽቱ ፋንታ ትቢያ ይሁ​ን​ብሽ፤ በወ​ርቅ መታ​ጠ​ቂ​ያ​ሽም ፋንታ ገመድ ታጠቂ፤ በራስ ወርቅ ቀጸ​ላ​ሽም ፋንታ ቡሃ​ነት ይው​ጣ​ብሽ፤ በሐር መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያሽ ፋንታ ማቅ ልበሽ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈውስ በሌ​ለው በግ​ብፅ ቍስል፥ በእ​ባ​ጭም፥ በቋ​ቁ​ቻም፥ በች​ፌም ይመ​ታ​ሃል።


ዐይ​ኖ​ች​ህም ከሚ​ያ​ዩት የተ​ነሣ ዕብድ ትሆ​ና​ለህ።


ፊተኛውም ሄዶ ጽዋውን በምድር ውስጥ አፈሰሰ፤ የአውሬውም ምልክት ባለባቸው ለምስሉም በሚሰግዱ ሰዎች ክፉኛ የሚነዘንዝ ቍስል ሆነባቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos