ዘፀአት 40:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሚቃጠል መሥዋዕትም የሚሆነውን መሠዊያ፥ ዕቃውንም ሁሉ ትቀባዋለህ፤ መሠዊያውንም ትቀድሳለህ፤ መሠዊያውም ቅዱሰ ቅዱሳን ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም የሚቃጠል መሥዋዕት መሠዊያውንና ዕቃዎቹን ሁሉ ቅባ፤ መሠዊያውን ቀድስ፣ እጅግም የተቀደሰ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሚቃጠል መሥዋዕት መሠዊያውንና ዕቃዎቹን ሁሉ ትቀባለህ፥ መሠዊያውንም ትቀድሳለህ፤ መሠዊያውም እጅግ የተቀደሰ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀጥሎም መሠዊያውን ከመገልገያ ዕቃዎቹ ጋር በመቀባት ለእግዚአብሔር የተለየ አድርገው፤ ፈጽሞም የተቀደሰ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆነውንም መሠዊያ ዕቃውንም ሁሉ ትቀባዋለህ፥ መሠዊያውንም ትቀድሳለህ፤ መሠዊያውም ቅድስተ ቅዱሳን ይሆናል። |
የእግዚአብሔር መንፈስ፥ የጥበብና የማስተዋል መንፈስ፥ የምክርና የኀይል መንፈስ፥ የዕውቀትና የእውነት መንፈስ ያርፍበታል።
የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶኛልና፤ ልባቸው የተሰበረውን እጠግን ዘንድ፥ ለተማረኩትም ነጻነትን፥ ለታሰሩትም መፈታትን፥ ለዕውራንም ማየትን እናገር ዘንድ ልኮኛል።
በእርሾ ቦክቶ አይጋገርም። ከእግዚአብሔር መሥዋዕት የሰጠኋቸው ዕድል ፈንታ ይህ ነው፤ እርሱም እንደ ኀጢአትና እንደ በደል መሥዋዕት ቅዱሰ ቅዱሳን ነው።
ይቀድሳቸውም ዘንድ መሠዊያውንና ዕቃውን ሁሉ፥ የመታጠቢያውን ሰንና መቀመጫውን ቀባ፤ ድንኳኒቱንና ዕቃዋን ሁሉ ቀብቶ ቀደሳቸው።
መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት፥ “መንፈስ ቅዱስ ያድርብሻል፤ የልዑል ኀይልም ይጋርድሻል፤ ከአንቺ የሚወለደውም ቅዱስ ነው፤ የልዑል እግዚአብሔር ልጅም ይባላል።
እናንተም በኢየሱስ ክርስቶስ ከእርሱ ናችሁ፤ በእርሱም ከእግዚአብሔር ጥበብንና ጽድቅን፥ ቅድስናንና ቤዛነትን አገኘን።
ቅዱስና ያለ ተንኰል፥ ነውርም የሌለበት፥ ከኀጢአተኞችም የተለየ፥ ከሰማያትም ከፍ ከፍ ያለ፥ እንደዚህ ያለ ሊቀ ካህናት ይገባናል።