ዘፀአት 4:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዲህ አሁን ሂድ፤ እኔም አንደበትህን አረታለሁ፤ ትናገረውም ዘንድ ያለህን አለብምሃለሁ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በል አሁን ሂድ፤ እኔ እንድትናገር አደርግሃለሁ፤ የምትናገረውንም አስተምርሃለሁ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ሂድ፥ እኔም ከአፍህ ጋር እሆናለሁ፥ የምትናገረውንም አስተምርሃለሁ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ አሁን ሂድ! እኔም ከአንተ ጋር ሆኜ መናገር እንድትችል አደርጋለሁ፤ ምን መናገር እንደሚገባህ እነግርሃለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ አሁን ሂድ፤ እኔም ከአፍህ ጋር እሆናለሁ፤ የምትናገረውንም አስተምርሃለሁ፤” አለው። |
እግዚአብሔርም ሙሴን ተናገረው፤ እንዲህ ሲል፥ “በእውነት እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ እኔም እንደ ላክሁህ ይህ ለአንተ ምልክት ይሆንሃል፤ ሕዝቡን ከግብፅ በአወጣህ ጊዜ በዚህ ተራራ ላይ እግዚአብሔርን ታመልካላችሁ” አለው።
አንተም ትናገረዋለህ፤ ቃሌንም በአፉ ታደርገዋለህ፤ እኔ አንደበትህንና አንደበቱን አረታለሁ፤ የምታደርጉትንም አለብማችኋለሁ።
አፌንም እንደ ተሳለ ሰይፍ አድርጎአል፤ በእጁ ጥላ ሰውሮኛል፤ እንደ ተሳለ ፍላጻም አድርጎኛል፤ በሰገባው ውስጥም ሸሽጎኛል።
የምናገረውን ቃል አውቅ ዘንድ ጌታ እግዚአብሔር የጥበብ ምላስን ሰጥቶኛል፤ ማለዳ ማለዳ ያነቃኛል፤ ለመስማትም ጆሮን ሰጥቶኛል።
ሲጐትቱአችሁና አሳልፈው ሲሰጡአችሁም ምን እንድትናገሩ አስቀድማችሁ አትጨነቁ፤ ዳሩ ግን በዚያች ሰዓት የሚሰጣችሁን ተናገሩ፤ የሚነግረው መንፈስ ቅዱስ ነው እንጂ እናንተ አይደላችሁምና።
ከዚህም በኋላ በአንዲት ቦታ ጸለየ፤ ጸሎቱን በጨረሰ ጊዜም ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ፥ “ጌታ ሆይ፥ ዮሐንስ ለደቀ መዛሙርቱ እንደ አስተማራቸው ጸሎት አስተምረን” አለው።
ነገር ግን አብ በስሜ የሚልከው የእውነት መንፈስ ጰራቅሊጦስ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል፤ እኔ የነገርኋችሁንም ሁሉ ያሳስባችኋል።
ከወንድሞቻቸው እንደ አንተ ያለ ነቢይ አስነሣላቸዋለሁ፤ ቃሌንም በአፉ አኖራለሁ፤ እንደ አዘዝሁትም ይነግራቸዋል፤