Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 49:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 አፌ​ንም እንደ ተሳለ ሰይፍ አድ​ር​ጎ​አል፤ በእጁ ጥላ ሰው​ሮ​ኛል፤ እንደ ተሳለ ፍላ​ጻም አድ​ር​ጎ​ኛል፤ በሰ​ገ​ባው ውስ​ጥም ሸሽ​ጎ​ኛል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 አፌን እንደ ተሳለ ሰይፍ አደረገው፤ በእጁ ጥላ ሰወረኝ፤ የተወለወለ ፍላጻ አደረገኝ፤ በሰገባውም ውስጥ ሸሸገኝ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 አፌንም እንደ ተሳለ ሰይፍ አድርጎአል፥ በእጁ ጥላ ሰውሮኛል፤ እንደ ተሳለ ፍላጻም አድርጎኛል፥ በሰገባውም ውስጥ ሸሽጎኛል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 አንደበቴን እንደ ሰይፍ የተሳለ አደረገው፤ በእጁ ጥላ ሥርም ሰወረኝ፤ እንደ ተሳለ ፍላጻ አድርጎ በሰገባው ውስጥ ደበቀኝ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 አፌንም እንደ ተሳለ ሰይፍ አድርጎአል፥ በእጁ ጥላ ሰውሮኛል፥ እንደ ተሳለ ፍላጻም አድርጎኛል፥ በሰገባውም ውስጥ ሸሽጎኛል።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 49:2
20 Referencias Cruzadas  

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ሕያው ነውና፤ የሚ​ሠ​ራም ሁለት ልሳን ካለው ሰይ​ፍም ሁሉ ይልቅ የተ​ሳለ ነው፤ ነፍ​ስ​ንና መን​ፈ​ስ​ንም፥ ጅማ​ት​ንና ቅል​ጥ​ም​ንም እስ​ኪ​ለይ ድረስ ይወ​ጋል፤ የል​ብ​ንም ስሜ​ትና አሳብ ይመ​ረ​ም​ራል።


በቀኝ እጁም ሰባት ከዋክብት ነበሩት፤ ከአፉም በሁለት ወገን የተሳለ ስለታም ሰይፍ ወጣ፤ ፊቱም በኀይል እንደሚበራ እንደ ፀሐይ ነበረ።


የም​ና​ገ​ረ​ውን ቃል አውቅ ዘንድ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የጥ​በብ ምላ​ስን ሰጥ​ቶ​ኛል፤ ማለዳ ማለዳ ያነ​ቃ​ኛል፤ ለመ​ስ​ማ​ትም ጆሮን ሰጥ​ቶ​ኛል።


ቃሌን በአ​ፍሽ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ሰማ​ይን በዘ​ረ​ጋ​ሁ​በ​ትና ምድ​ርን በመ​ሠ​ረ​ት​ሁ​በት በእጄ ጥላ እጋ​ር​ድ​ሻ​ለሁ፤ ጽዮ​ን​ንም አንቺ ሕዝቤ ነሽ እላ​ታ​ለሁ።


“በጴርጋሞንም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፡ በሁለት ወገን የተሳለ ስለታም ሰይፍ ያለው እንዲህ ይላል፦


እነሆ በም​ድ​ሪቱ ሁሉ ላይ፥ በይ​ሁ​ዳም ነገ​ሥ​ታት በአ​ለ​ቆ​ች​ዋና በካ​ህ​ናቷ ላይ፥ በም​ድ​ሪ​ቱም ሕዝብ ላይ እንደ ተመ​ሸ​ገች ከተማ፥ እንደ ብረ​ትም ዓምድ፥ እንደ ናስም ቅጥር ዛሬ አድ​ር​ጌ​ሃ​ለሁ።


ነገር ግን ለድ​ሆች በጽ​ድቅ ይፈ​ር​ዳል፤ ለም​ድ​ርም የዋ​ሆች በቅ​ን​ነት ይበ​ይ​ናል፤ በአ​ፉም ቃል ምድ​ርን ይመ​ታል፤ በከ​ን​ፈ​ሩም እስ​ት​ን​ፋስ ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውን ያጠ​ፋ​ዋል።


ስለ​ዚህ ነቢ​ያ​ቶ​ቻ​ች​ሁን አጨ​ድ​ኋ​ቸው፤ በአ​ፌም ቃል ገደ​ል​ኋ​ቸው፤ ፍር​ዴም እንደ ብር​ሃን ይወ​ጣል።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መታ​መን ይሻ​ላል፥ ልዑል ሆይ፥ ለስ​ም​ህም መዘ​መር፤


አሕዛብንም ይመታበት ዘንድ ስለታም ሰይፍ ከአፉ ይወጣል፤ እርሱም በብረት በትር ይገዛቸዋል፤ እርሱም ሁሉን የሚገዛ የእግዚአብሔርን የብርቱ ቍጣውን ወይን መጥመቂያ ይረግጣል።


ያን​ጊ​ዜም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ድም​ፁን ከፍ አድ​ርጎ፥ “አባት ሆይ፥ ነፍ​ሴን በአ​ንተ እጅ አደራ እሰ​ጣ​ለሁ” ብሎ ጮኸ፤ ይህ​ንም ብሎ ነፍ​ሱን ሰጠ።


እነሆ፥ ደግፌ የያ​ዝ​ሁት ባሪ​ያዬ ያዕ​ቆብ፤ ነፍሴ የተ​ቀ​በ​ለ​ችው ምርጤ እስ​ራ​ኤ​ልም፤ በእ​ርሱ ላይ መን​ፈ​ሴን አድ​ር​ጌ​አ​ለሁ፤ እር​ሱም ለአ​ሕ​ዛብ ፍር​ድን ያመ​ጣል።


የመ​ዳ​ን​ንም የራስ ቍር በራ​ሳ​ችሁ ላይ ጫኑ፤ የመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስ​ንም ሰይፍ ያዙ፤ ይኸ​ውም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ነው።


እንግዲህ ንስሓ ግባ፤ አለዚያ ፈጥኜ እመጣብሃለሁ፤ በአፌም ሰይፍ እዋጋቸዋለሁ።


ክብ​ሬም በአ​ለፈ ጊዜ በአ​ለቱ ስን​ጥቅ ውስጥ አኖ​ር​ሃ​ለሁ፤


ከእ​ና​ንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈራ፥ ማን ነው? የባ​ሪ​ያ​ው​ንም ቃል ይስማ፤ በጨ​ለ​ማም የም​ት​ሄዱ፥ ብር​ሃ​ንም የሌ​ላ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ታመኑ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተደ​ገፉ፤


ፍላጾችህ ከወጡበት ብርሃን የተነሣ፥ ከሚንቦገቦገውም ከጦርህ ፀዳል የተነሣ፥ ፀሐይና ጨረቃ በመኖሪያቸው ቆሙ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios