ዘፀአት 39:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው እርስዋን ከወርቅ፥ ከሰማያዊና ከሐምራዊ፥ ከቀይ ግምጃም፥ ከተፈተለ ከጥሩ በፍታም እንደ ሠሩ የልብሰ መትከፉን ቋድ ሠሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጥበብ የተፈተለው መታጠቂያ በተመሳሳይ መልክ ሆኖ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው፣ ከኤፉዱ ጋራ አንድ ወጥ የሆነና ከወርቅ፣ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊና ከቀይ ማግ፣ በቀጭኑ ከተፈተለ ሐር የተሠራ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በላዩም መታጠቂያ ሆኖ በብልሃት የተጠለፈው የኤፉዱ ቋድ እንደ እርሱ ከወርቅ፥ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊ፥ ከቀይ ግምጃና ከተፈተለ ጥሩ በፍታ የተሠራ ነበረ፥ ጌታ ሙሴን እንዳዘዘው ከእርሱ ጋር ወጥ ሆኖ የተሠራ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ከወርቅ ክር፥ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና፥ ከቀይ ከፈይ ከተፈተለ ጥሩ በፍታ በብልኀት የተጠለፈው ቀበቶ አንድ ወጥ በመሆን ከኤፉዱ ጋር ተያይዞ ተሠራ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በላዩም መታጠቂያ ሆኖ በብልሃት የተጠለፈው የኤፉዱ ቍድ እንደ እርሱ ከእርሱም ጋር አንድ ነበረ፤ ከወርቅና ከሰማያዊ ከሐምራዊ ከቀይ ግምጃም ከተፈተለም ከጥሩ በፍታ የተሠራ ነበረ። |
በላዩም የተጠለፈው የልብሰ መትከፍ ቋድ እንደ እርሱ፥ ከእርሱም ጋር አንድ ይሁን፤ ከወርቅ፥ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊ፥ ከቀይ ግምጃም ከተፈተለ፥ ከጥሩ በፍታም የተሠራ ይሁን።
ልብሶችን ወስደህ ለወንድምህ ለአሮን የነጭ ሐር እጀ ጠባብ ቀሚስ፥ ልብሰ መትከፍና ልብሰ እንግድዓ ታለብሰዋለህ፤ ለእርሱም ልብሰ እንግድዓውን ከልብሰ መትከፉ ጋር አያይዝለት።
እጀ ጠባብም አለበሰው፤ በመታጠቂያም አስታጠቀው፤ የበፍታ ቀሚስም አለበሰው፤ ልብሰ መትከፍም ደረበለት፤ በልብሰ መትከፉም አሠራር ላይ በብልሃት በተጠለፈ ቋድ አስታጠቀውና በእርሱ ላይ አሰረው።
ከእግዚአብሔር እንደ ተማርሁ አስተምሬአችኋለሁና፤ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱን ራሱን በያዙባት በዚያች ሌሊት ኅብስቱን አነሣ።