Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 28:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 በላ​ዩም የተ​ጠ​ለ​ፈው የል​ብሰ መት​ከፍ ቋድ እንደ እርሱ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር አንድ ይሁን፤ ከወ​ርቅ፥ ከሰ​ማ​ያዊ፥ ከሐ​ም​ራዊ፥ ከቀይ ግም​ጃም ከተ​ፈ​ተለ፥ ከጥሩ በፍ​ታም የተ​ሠራ ይሁን።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 በጥበብ የተጠለፈው የወገብ መታጠቂያ ከወርቅ፣ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና በቀጭኑ ከተፈተለ ሐር ከኤፉድ ጋራ አንድ ወጥ ሆኖ የተሠራ ይሁን።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 በላዩ ያለው በብልሃት የተጠለፈው የኤፉዱ መታጠቂያ ከእርሱ ጋር ወጥ ሆኖ ከወርቅ፥ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊ፥ ከቀይ ግምጃና ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ የተሠራ ይሁን።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ኤፉዱ ከተሠራባቸው ተመሳሳይ ነገሮች በብልኀት የተጠለፈ መታጠቂያ አንድ ላይ እንደ ተሠራ ሆኖ ከኤፉዱ ጋር ይጣበቅ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 በላዩም መታጠቂያ ሆኖ በብልሃት የተጠለፈው የኤፉድ ቍድ እንደ እርሱ ከእርሱም ጋር አንድ ይሁን፤ ከወርቅና ከሰማያዊ ከሐምራዊ ከቀይ ግምጃም ከተፈተለ ከጥሩ በፍታም የተሠራ ይሁን።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 28:8
10 Referencias Cruzadas  

ሁለቱ ወገን አንድ እን​ዲ​ሆን በሁ​ለቱ ጫንቃ ላይ የሚ​ጋ​ጠም ጨርቅ ይሁን።


ሁለ​ትም የመ​ረ​ግድ ድን​ጋይ ወስ​ደህ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ስም ስማ​ቸ​ውን ቅረ​ጽ​ባ​ቸው፤


ልብ​ሶ​ችን ወስ​ደህ ለወ​ን​ድ​ምህ ለአ​ሮን የነጭ ሐር እጀ ጠባብ ቀሚስ፥ ልብሰ መት​ከ​ፍና ልብሰ እን​ግ​ድዓ ታለ​ብ​ሰ​ዋ​ለህ፤ ለእ​ር​ሱም ልብሰ እን​ግ​ድ​ዓ​ውን ከል​ብሰ መት​ከፉ ጋር አያ​ይ​ዝ​ለት።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው እር​ስ​ዋን ከወ​ርቅ፥ ከሰ​ማ​ያ​ዊና ከሐ​ም​ራዊ፥ ከቀይ ግም​ጃም፥ ከተ​ፈ​ተለ ከጥሩ በፍ​ታም እንደ ሠሩ የል​ብሰ መት​ከ​ፉን ቋድ ሠሩ።


ወገ​ቡን በጽ​ድቅ ይታ​ጠ​ቃል፤ እው​ነ​ት​ንም በጎኑ ይጐ​ና​ጸ​ፋል።


እጀ ጠባ​ብም አለ​በ​ሰው፤ በመ​ታ​ጠ​ቂ​ያም አስ​ታ​ጠ​ቀው፤ የበ​ፍታ ቀሚ​ስም አለ​በ​ሰው፤ ልብሰ መት​ከ​ፍም ደረ​በ​ለት፤ በል​ብሰ መት​ከ​ፉም አሠ​ራር ላይ በብ​ል​ሃት በተ​ጠ​ለፈ ቋድ አስ​ታ​ጠ​ቀ​ውና በእ​ርሱ ላይ አሰ​ረው።


ስለዚህ የልቡናችሁን ወገብ ታጥቃችሁና በመጠን ኖራችሁ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ የምታገኙትን ጸጋ ፈጽማችሁ ተስፋ አድርጉ።


በመቅረዞቹም መካከል የሰው ልጅ የሚመስለውን አየሁ፤ እርሱም እስከ እግሩ ድረስ ልብስ የለበሰ ደረቱንም በወርቅ መታጠቂያ የታጠቀ ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos