ዘፀአት 39:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቀረውም የመባ ወርቅ በእግዚአብሔር ፊት ይሠሩበት ዘንድ ንዋየ ቅድሳት ሆኖ ተሠራ። ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊም ከቀይ ግምጃም ለመቅደሱ አገልግሎት ልብሶችን ሠሩ፤ እንዲሁም እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው ለአሮን የተቀደሰውን ልብስ ሠሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለመቅደሱ አገልግሎት ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊና ከቀይ ማግ የተፈተሉ ልብሶችን ሠሩ፤ እንዲሁም እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው ለአሮን የተቀደሱ ልብሶችን ሠሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመቅደሱ ለማገልገል ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ግምጃ በብልሃት የተሠራ ልብስ አደረጉ፥ ጌታም ሙሴን ባዘዘው መሠረት ለአሮን የተቀደሱ ልብሶችን ሠሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ካህናቱ በተቀደሰው ስፍራ ሲያገለግሉ የሚለብሱአቸውን እጅግ የተዋቡትን የካህናት ልብሶች ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ከፈይ ሠሩ፤ የአሮንንም የክህነት ልብሶች እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ሠሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው፥ በመቅደሱ ለማገልገል ከሰማያዊ ከሐምራዊም ከቀይ ግምጃም በብልሃት የተሠራ ልብስ፥ ለአሮንም የተቀደሰውን ልብስ አደረጉ። |
“ለድንኳኑም ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ፥ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊም፥ ከቀይም ግምጃ ዐሥር መጋረጆችን ሥራ፤ ኪሩቤልም በእነርሱ ላይ ይሁኑ፤ እንደ ሽመና ሥራም በብልሃት ትሠራቸዋለህ።
በመቅደስ ውስጥ ለማገልገል በብልሃት የተሠሩትን ልብሶች፥ በክህነት ያገለግሉበት ዘንድ የተቀደሱትን የካህኑን የአሮንን ልብሶች፥ የልጆቹንም ልብሶች።”
ሰማያዊም፥ ሐምራዊም፥ ቀይ ግምጃም፥ የተፈተለ በፍታም፥ የፍየል ጠጕርም፥ ቀይ የአውራ በግ ቍርበትም፥ የአቆስጣ ቍርበትም ያላቸው ሰዎች ሁሉ አመጡ።
በአደባባዩ ዙሪያ ያሉትን እግሮች፥ የአደባባዩንም ደጃፍ እግሮች፥ የድንኳኑንም ካስማዎች ሁሉ፥ በአደባባዩ ዙሪያም ያሉትን ካስማዎች ሁሉ አደረገ።
በመቅደስ ውስጥ ለማገልገል በብልሃት የተሠሩትን ልብሶች፥ በክህነትም ያገለግሉበት ዘንድ የተቀደሱትን የካህኑን የአሮንን ልብሶች፥ የልጆቹንም ልብሶች አመጡ።
ካህናቱም በገቡ ጊዜ ከመቅደሱ በውጭው አደባባይ አይወጡም፤ የሚያገለግሉበትን ልብሳቸውን ግን ቅዱስ ነውና በዚያ ያኖሩታል፤ ሌላም ልብስ ለብሰው ወደ ሕዝብ ይወጣሉ።”
በተራራው ራስ ላይ ያለውን ቤቱንና የቤቱን ሥርዐት ሣል፤ የዙሪያውም ዳርቻ ሁሉ ቅዱሰ ቅዱሳን ነው። እነሆ የቤቱ ሕግ ይህ ነው።”