Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 39:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ካህናቱ በተቀደሰው ስፍራ ሲያገለግሉ የሚለብሱአቸውን እጅግ የተዋቡትን የካህናት ልብሶች ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ከፈይ ሠሩ፤ የአሮንንም የክህነት ልብሶች እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ሠሩ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ለመቅደሱ አገልግሎት ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊና ከቀይ ማግ የተፈተሉ ልብሶችን ሠሩ፤ እንዲሁም እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው ለአሮን የተቀደሱ ልብሶችን ሠሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 በመቅደሱ ለማገልገል ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ግምጃ በብልሃት የተሠራ ልብስ አደረጉ፥ ጌታም ሙሴን ባዘዘው መሠረት ለአሮን የተቀደሱ ልብሶችን ሠሩ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 የቀ​ረ​ውም የመባ ወርቅ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ይሠ​ሩ​በት ዘንድ ንዋየ ቅድ​ሳት ሆኖ ተሠራ። ከሰ​ማ​ያዊ፥ ከሐ​ም​ራ​ዊም ከቀይ ግም​ጃም ለመ​ቅ​ደሱ አገ​ል​ግ​ሎት ልብ​ሶ​ችን ሠሩ፤ እን​ዲ​ሁም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው ለአ​ሮን የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን ልብስ ሠሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው፥ በመቅደሱ ለማገልገል ከሰማያዊ ከሐምራዊም ከቀይ ግምጃም በብልሃት የተሠራ ልብስ፥ ለአሮንም የተቀደሰውን ልብስ አደረጉ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 39:1
14 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር ሆይ! ሕግህ ጽኑ ነው፤ መቅደስህም ለዘለዓለም ያማረና ቅዱስ ነው።


ሰማያዊና ሐምራዊ፥ ቀይም ከፈይ፥ ጥሩ በፍታ፥ ከፍየል ጠጒር የተሠራ ልብስ፥


“እንዲሁም የተቀደሰውን ድንኳን ውስጠኛ ክፍል ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ከፈይ ከተፈተለ በፍታ በተሠሩ ዐሥር መጋረጃዎች አብጀው፤ በእነርሱም ላይ ኪሩቤል በጥልፍ ጥበብ እንዲሳሉ አድርግ።


ጥበበኞቹም ልብሶቹን ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊ፥ ከቀይ ከፈይ ከወርቅ ምዝምዝና ከጥሩ በፍታ በጥልፍ አስጊጠው ይሥሩ።


አሮንና ልጆቹ በክህነት አገልግሎት ላይ ሲሆኑ የሚጠቀሙባቸው የተዋቡ አልባሳት፥


ካህናቱ በተቀደሰው ስፍራ በሚያገለግሉበት ጊዜ የሚለብሱአቸው በጥበብ ያጌጡ ልብሶችን ይኸውም ለካህኑ ለአሮንና ለልጆቹ የተሠሩትን የተቀደሱ ልብሶች ይሥሩ።”


ጥሩ በፍታ፥ ሰማያዊ፥ ሐምራዊና ቀይ ከፈይ ከፍየል ጠጒር የተሠራ ልብስ፥ ቀይ ቀለም የተነከረ የአውራ በግ ቆዳ፤ እንዲሁም የለፋ ቊርበት ያለው ሁሉ ይዞ መጣ።


በዙሪያ ያለው የአደባባይ አጥርና ወደ አደባባዩ የሚያስገባው ደጃፍ የሚቆሙባቸውን እግሮች፥ እንዲሁም የድንኳኑና በዙሪያው ያለውን የአደባባይ አጥር ካስማዎችን ሁሉ ሠራ።


ካህኑ አሮንና ልጆቹ በተቀደሰው ስፍራ በክህነት ሲያገለግሉ የሚለብሱአቸው የተቀደሱና ውብ የሆኑ የክህነት አልባሳት ናቸው።


ካህናቱ ወደተቀደሰው ቦታ ገብተው የሚያገለግሉባቸውን ልብሶች ከለበሱ በኋላ ያን ያገልግሎት ልብስ ሳያወልቁ ወደ ውጪው አደባባይ አይወጡም፤ ልብሶቹም የተቀደሱ ስለ ሆኑ ከተቀደሰው ቦታ ወጥተው ለሕዝብ ወደተፈቀደው ቦታ ከመድረሳቸው በፊት ሌላ ልብስ መልበስ ይኖርባቸዋል።”


የቤተ መቅደሱም ሕግ ይህ ነው፤ በተራራው ጫፍ ላይ በቤተ መቅደሱ ዙሪያ ያለው ክልል በሙሉ እጅግ የተቀደሰ ይሆናል።”


እርሱ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን አንዴ በማያዳግም ሁኔታ የራሱን ደም ይዞ ገባ እንጂ የፍየሎችንና የወይፈኖችን ደም ይዞ አልገባም፤ በዚህም ዐይነት የዘለዓለም ቤዛን አስገኘልን።


የአይሁድ የካህናት አለቃ የራሱ ያልሆነውን ደም ይዞ በየዓመቱ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ይገባ ነበር፤ ክርስቶስ ግን ራሱን ብዙ ጊዜ መሥዋዕት አድርጎ ለማቅረብ አልገባም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos