የሆርም ልጅ የኡሪ ልጅ ባስልኤል የሠራው የናስ መሠዊያ በዚያ በእግዚአብሔር ማደሪያ ፊት ነበረ፤ ሰሎሞንና የእስራኤልም ጉባኤ የእግዚአብሔርን ታቦት ይፈልጓት ነበር።
ዘፀአት 38:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ርዝመቱ አምስት ክንድ፥ ወርዱም አምስት ክንድ ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆን መሠዊያን ከማይነቅዝ ዕንጨት አደረገ፤ አራት ማዕዘንም ነበረ፤ ከፍታውም ሦስት ክንድ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከፍታው ሦስት ክንድ የሆነ የሚቃጠል መሥዋዕት መሠዊያ ከግራር ዕንጨት ሠሩ፤ ርዝመቱ ዐምስት ክንድ፣ ወርዱ ዐምስት ክንድ የሆነ ባለአራት ማእዘን ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሚቃጠል መሥዋዕት መሠዊያ ከግራር እንጨት ሠራ፤ እርሱም ርዝመቱ አምስት ክንድ፥ ወርዱ አምስት ክንድ ነበር፥ አራት ማዕዘንም ነበረ፥ ከፍታው ሦስት ክንድ ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሚቃጠል መሥዋዕት መሠዊያ ከግራር እንጨት ሠራ፤ እርሱም አራት ማእዘን ሆኖ ሁለት ሜትር ከኻያ ሳንቲ ሜትር ርዝመት፥ ሁለት ሜትር ከኻያ ሳንቲ ሜትር ስፋት፥ አንድ ሜትር ከሠላሳ ሳንቲ ሜትር ቁመት ነበረው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ርዝመቱ አምስት ክንድ፥ ወርዱም አምስት ክንድ ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆን መሠዊያን ከግራር እንጨት አደረገ፤ አራት ማዕዘንም ነበረ፤ ከፍታው ሦስት ክንድ ነበረ። |
የሆርም ልጅ የኡሪ ልጅ ባስልኤል የሠራው የናስ መሠዊያ በዚያ በእግዚአብሔር ማደሪያ ፊት ነበረ፤ ሰሎሞንና የእስራኤልም ጉባኤ የእግዚአብሔርን ታቦት ይፈልጓት ነበር።
ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆነውን መሠዊያም በምስክሩ ድንኳን ደጅ አኖረ፤ እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው በላዩ መሥዋዕቱንና ቍርባኑን አቀረበ።
ወንድሞቻችን፥ ሰውነታችሁን ለእግዚአብሔር ሕያውና ቅዱስ፥ ደስ የሚያሰኝም መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እማልዳችኋለሁ። ይህም በዕውቀት የሚሆን አገልግሎታችሁ ነው።
አሁንም ከሰማያዊ ጥሪ ተካፋዮች የሆናችሁ ቅዱሳን ወንድሞቻችን ሆይ፥ የሃይማኖታችንን ሐዋርያና ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስን ተመልከቱ።
ነውር የሌለው ሆኖ፥ በዘለዓለም መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበ የክርስቶስ ደም ሕያው እግዚአብሔርን እናመልከው ዘንድ ሕሊናችንን ከሞት ሥራ እንዴት ይልቅ ያነጻ ይሆን?
እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ።
ከተማይቱም አራት ማዕዘን ነበራት፤ ርዝመትዋም እንደ ስፋትዋ ልክ ነበረ። ከተማይቱንም በዘንግ ለካት፤ ሁለት ሺህ አራት መቶ ኪሎ ሜትር ሆነች፤ ርዝመትዋና ስፋትዋ ከፍታዋም ትክክል ነው።