ዳዊትም የገባዖንን ሰዎች፥ “የእግዚአብሔርን ርስት ትባርኩ ዘንድ ምን ላድርግላችሁ? ማስተስረያውስ ምንድን ነው?” አላቸው።
ዘፀአት 30:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለነፍሳችሁ ቤዛ የእግዚአብሔርን ስጦታ ስትሰጡ ባለ ጠጋው ከሰቅል ግማሽ አይጨምር፤ ድሃውም አያጕድል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለሕይወታችሁ ማስተስረያ እንዲሆን ለእግዚአብሔር መሥዋዕት በምታቀርቡበት ጊዜ ባለጠጋው ከግማሽ ሰቅል በላይ፣ ድኻውም አጕድሎ አይስጥ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለነፍሳችሁ ማስተስረያ የጌታን ስጦታ ስትሰጡ፥ ከግማሽ ሰቅሉ ባለ ጠጋው አይጨምር፥ ደሃውም አያጉድል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለሕይወታቸው ቤዛ ይህን መባ ሲያቀርቡ ሀብታሙም ሆነ ድኻው እኩል ይክፈል እንጂ የሀብታሙ ክፍያ ብዙ የድኻው ክፍያ አነስተኛ አይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለነፍሳችሁ ማስተስረያ የእግዚአብሔርን ስጦታ ስትሰጡ ባለ ጠጋው ከሰቅል ግማሽ አይጨምር፥ ደሀውም አያጉድል። |
ዳዊትም የገባዖንን ሰዎች፥ “የእግዚአብሔርን ርስት ትባርኩ ዘንድ ምን ላድርግላችሁ? ማስተስረያውስ ምንድን ነው?” አላቸው።
“አንተ የእስራኤልን ልጆች ቍጥር የወሰድህ እንደ ሆነ በቈጠርሃቸው ጊዜ መቅሠፍት እንዳይሆንባቸው፥ በቈጠርሃቸው ጊዜ ከእነርሱ ሰው ሁሉ እንደ ቍጥራቸው መጠን የነፍሱን ቤዛ ለእግዚአብሔር ይስጥ።
የማስተስረያውንም ገንዘብ ከእስራኤል ልጆች ወስደህ ለምስክሩ ድንኳን ማገልገያ ትሰጠዋለህ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ለነፍሳችሁ ቤዛ እንዲሆን ለእስራኤል ልጆች መታሰቢያ ይሁን።”
እያንዳንዱም ሰው አንድ አንድ ዲድርክም አዋጣ፤ አንድ ዲድርክም እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን የሰቅል ግማሽ ነው፤ ይህም የተዋጣው ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ከተቈጠሩ ሁሉ ስድስት መቶ ሦስት ሺህ አምስት መቶ አምሳ ሰዎች ነበረ።
የሥጋ ሁሉ ሕይወት ደሙ ነው፤ ደሙም ከሕይወቱ የተነሣ ያስተሰርያልና በመሠዊያው ላይ ለነፍሳችሁ ማስተስረያ ይሆን ዘንድ እኔ ለእናንተ ሰጠሁት።
ሰውም ሁሉ ከአገኘው ከወርቅ ዕቃ፥ ከእግር አልቦም፥ ከአምባርም፥ ከቀለበትም ከጕትቻም፥ ከድሪውም ስለ እኛ በእግዚአብሔር ፊት ታስተሰርዩልን ዘንድ ለእግዚአብሔር መባ አምጥተናል” አሉት።
እናንተም ጌቶች ሆይ፥ ቍጣችሁን እያበረዳችሁ፥ በደላቸውንም ይቅር እያላችሁ፥ ትክክለኛውን አድርጉላቸው፤ ፊት አይቶ የማያዳላ ጌታ በእነርሱና በእናንተ ላይ በሰማይ እንደ አለ ታውቃላችሁና።