Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፀአት 30:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 የማ​ስ​ተ​ስ​ረ​ያ​ው​ንም ገን​ዘብ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ወስ​ደህ ለም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ማገ​ል​ገያ ትሰ​ጠ​ዋ​ለህ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ለነ​ፍ​ሳ​ችሁ ቤዛ እን​ዲ​ሆን ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መታ​ሰ​ቢያ ይሁን።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 የማስተስረያውን ገንዘብ ከእስራኤላውያን ተቀብለህ ለመገናኛው ድንኳን አገልግሎት አውለው፤ ለሕይወታችሁ ማስተስረያ በማድረግ በእግዚአብሔር ፊት የእስራኤላውያን ማስተስረያ ይሆናል።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 የማስተስረያውን ገንዘብ ከእስራኤል ልጆች ወስደህ ለመገናኛው ድንኳን አገልግሎት ስጠው፤ ለእስራኤል ልጆች ለነፍሳችሁ ቤዛ እንዲሆን በጌታ ፊት መታሰቢያ ይሆናል።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ይህን መባ ከእስራኤል ሕዝብ ሰብስበህ ለተቀደሰው ድንኳን መንከባከቢያ እንዲውል አድርግ፤ ይህም መባ ለሕይወታቸው ቤዛ ይሆናል፤ እኔም እጠብቃቸው ዘንድ እነርሱን አስታውሳለሁ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 የማስተስረያውንም ገንዘብ ከእስራኤል ልጆች ወስደህ ለመገናኛው ድንኳን ማገልገያ ታደርገዋለህ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ለነፍሳችሁ ቤዛ እንዲሆን ለእስራኤል ልጆች መታሰቢያ ይሁን።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 30:16
9 Referencias Cruzadas  

እንደ ቆሬና ከእ​ር​ሱም ጋር እንደ ተቃ​ወ​ሙት ሰዎች እን​ዳ​ይ​ሆን፥ ከአ​ሮን ልጆች ያል​ሆነ ሌላ ሰው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ዕጣን ያጥን ዘንድ እን​ዳ​ይ​ቀ​ርብ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሙሴ ቃል እንደ ተና​ገ​ረው፥ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መታ​ሰ​ቢያ አደ​ረ​ጋ​ቸው።


ይህም ቀን መታ​ሰ​ቢያ ይሁ​ና​ችሁ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዓል ታደ​ር​ጉ​ታ​ላ​ችሁ፤ ለልጅ ልጃ​ች​ሁም ሥር​ዐት ሆኖ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ታደ​ር​ጉ​ታ​ላ​ችሁ።


ኅብ​ስ​ቱ​ንም አነሣ፤ አመ​ስ​ገነ፤ ፈት​ቶም ሰጣ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ስለ እና​ንተ ቤዛ ሆኖ የሚ​ሰጥ ሥጋዬ ይህ ነው፤ ይህ​ንም ለመ​ታ​ሰ​ቢ​ያዬ አድ​ር​ጉት፤”


ለነ​ፍ​ሳ​ችሁ ቤዛ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስጦታ ስት​ሰጡ ባለ ጠጋው ከሰ​ቅል ግማሽ አይ​ጨ​ምር፤ ድሃ​ውም አያ​ጕ​ድል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦


ሙሴና ካህኑ አል​ዓ​ዛ​ርም ወር​ቁን ከሻ​ለ​ቆ​ችና ከመቶ አለ​ቆች ወሰዱ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መታ​ሰ​ቢያ ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን አገ​ቡት።


ንጉሡ ኢዮ​አ​ስም አለ​ቃ​ውን ኢዮ​አ​ዳን ጠርቶ፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባሪያ ሙሴ እስ​ራ​ኤ​ልን በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን በሰ​በ​ሰበ ጊዜ እን​ዲ​ያ​ዋጣ ያዘ​ዘ​ውን ግብር ከይ​ሁ​ዳና ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ያመጡ ዘንድ ስለ ምን ሌዋ​ው​ያ​ንን አል​ተ​ከ​ታ​ተ​ል​ህም?” አለው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios