በምስክሩ ድንኳን ውስጥ በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ካለው መጋረጃ ውጭ አሮንና ልጆቹ ከማታ እስከ ማለዳ ድረስ በእግዚአብሔር ፊት ያብሩት፤ በእስራኤል ልጆች ዘንድ ለልጅ ልጃቸው የዘለዓለም ሥርዐት ይሁን።
ዘፀአት 29:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመታጠቂያም ታስታጥቃቸዋለህ፤ ቆብንም ታደርግላቸዋለህ፤ ለዘለዓለም ሥርዐትም ክህነት ይሆንላቸዋል፤ እንዲሁም የአሮንንና የልጆቹን እጆች ትቀባቸዋለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የራስ ማሰሪያዎችንም አድርግላቸው፤ ከዚያም አሮንንና ወንዶች ልጆቹን መታጠቂያዎችን አስታጥቃቸው፤ ክህነት የዘላለም ሥርዐት ይሆንላቸዋል። “በዚህም መንገድ አሮንንና ወንዶች ልጆቹን ትክናቸዋለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሮንንና ልጆቹን በመታጠቂያ ታስታጥቃቸዋለህ፥ ቆብን ታለብሳቸዋለህ፤ ክህነትም ለዘለዓለም ለእነርሱ የተወሰነ ይሆናል፥ እንዲሁም አሮንን እጅና የልጆቹን እጅ ትቀድሳለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለወገባቸውም መታጠቂያ አድርግላቸው፤ በራሳቸውም ላይ ቆብ ድፋላቸው፤ ክህነታቸው ለዘለዓለም ቋሚ ሥርዓት ይሆናል፤ በዚህም ዐይነት አሮንንና ልጆቹን ትሾማለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሮንንና ልጆቹንም በመታጠቂያ ታስታጥቃቸዋለህ፥ ቆብንም ታለብሳቸዋለህ፤ ለዘላለም ሥርዓትም ክህነት ይሆንላቸዋል፤ እንዲሁም አሮንንና ልጆቹን ትክናቸዋለህ። |
በምስክሩ ድንኳን ውስጥ በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ካለው መጋረጃ ውጭ አሮንና ልጆቹ ከማታ እስከ ማለዳ ድረስ በእግዚአብሔር ፊት ያብሩት፤ በእስራኤል ልጆች ዘንድ ለልጅ ልጃቸው የዘለዓለም ሥርዐት ይሁን።
“አንተም ወንድምህን አሮንን ከእርሱም ጋር ልጆቹን ከእስራኤል ልጆች መካከል ለይተህ በክህነት ያገለግሉኝ ዘንድ ወደ አንተ አቅርብ፤ አሮንን የአሮንንም ልጆች፥ ናዳብን፥ አብዩድንም፥ አልዓዛርንም ኢታምርንም አቅርብ።
ሙሴም፥ “ዛሬ በረከትን እንዲያወርድላችሁ ከእናንተ እያንዳንዱ ከልጁና፥ ከወንድሙ የተነሣ እግዚአብሔርን በእጃችሁ ደስ አሰኛችሁት” አላቸው።
አባታቸውን እንደ ቀባህ ትቀባቸዋለህ፤ ካህናትም ይሆኑኛል። ይህም ለልጅ ልጃቸው ለዘለዓለም የክህነት ቅብዐት ይሆንላቸዋል።”
እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው ሙሴ የአሮንን ልጆች አቀረበ፤ የበፍታ ቀሚሶችንም አለበሳቸው፤ በመታጠቂያም አስታጠቃቸው፤ አክሊልም ደፋላቸው።
አንተን ከአንተም ጋር የሌዊን ልጆች ወንድሞችህን ሁሉ ወደ እርሱ አቅርቦአል፤ ካህናትም ትሆኑ ዘንድ ትፈልጋላችሁን?
እንደ ቆሬና ከእርሱም ጋር እንደ ተቃወሙት ሰዎች እንዳይሆን፥ ከአሮን ልጆች ያልሆነ ሌላ ሰው በእግዚአብሔር ፊት ዕጣን ያጥን ዘንድ እንዳይቀርብ፥ እግዚአብሔር በሙሴ ቃል እንደ ተናገረው፥ ለእስራኤል ልጆች መታሰቢያ አደረጋቸው።
አንተም ከአንተም ጋር ልጆችህ እንደ መሠዊያውና፥ በመጋረጃውም ውስጥ እንዳለው ሥርዐት ሁሉ ክህነታችሁን ጠብቁ፤ የሀብተ ክህነት አገልግሎታችሁንም አድርጉ፤ ከሌላም ወገን የሆነ ሰው ቢቀርብ ይገደል።”
ለአምላኩ ቀንቶአልና፥ ለእስራኤልም ልጆች አስተስርዮአልና፥ ለእርሱ ከእርሱም በኋላ ለዘሩ ለዘለዓለም የክህነት ቃል ኪዳን ይሆንለታል።”
አሮንንና ልጆቹን በምስክሩ ድንኳን ፊት አቁማቸው፤ ክህነታቸውንም፥ በመሠዊያውና በመጋረጃው ውስጥ ያለውንም ሁሉ ይጠብቁ፤ ከሌላ ወገን የዳሰሰ ቢኖር ይገደል።”
እርሱ ከልጆቹ ጋር በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ቁሞ ለዘለዓለም ያገለግል ዘንድ፥ በስሙም ይባርክ ዘንድ አምላክህ እግዚአብሔር ከነገዶችህ ሁሉ መርጦታልና።
ስለዚህም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በእውነት ቤትህ፥ የአባትህም ቤት፤ ለዘለዓለም በፊቴ እንዲኖር ተናግሬአለሁ፤ አሁን ግን እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ያከበሩኝን አከብራለሁና፥ የናቁኝም ይናቃሉና ይህ አይሆንልኝም።